የዲሲፕሊን ውሳኔዎች
1. ዘረሰናይ ብርሃነ (መቐለ 70 እንደርታ): ክለቡ ከ ሲዳማ ቡና ጋር ባደረገው የ6ኛ ሳምንት እግርኳስ ጨዋታ በ 75 ኛ ደቂቃ ላይሁለተኛ ቢጫ ካርድ የሚያስጥ ጥፋት በመፈፀማቸው በቀይ ካርድ ከጨዋታ ሜዳ የተወገደ ስለመሆኑ ሪፖርት ቀርቦበታል ።
ስለሆነም ተጫዋቹ ለፈፀመው ጥፋት በኢ.እ.ፌ ዲሲፕሊን መመሪያ ክፍል 2 ምዕራፍ 2 አንቀፅ 35(መ) መሰረት 1 ጨዋታ እንዲታገድ የየውድድርና ስነስርዓት ኮሚቴ ወስኗል፡፡
2. አካሉ አቲሞ (አርባምንጭ ከተማ): ክለቡ ከ ሸገር ከተማ ጋር ባደረገው የ6ኛ ሳምንትእግርኳስ ጨዋታ በ 90+5 ኛ ደቂቃ ላይሁለተኛ ቢጫ ካርድ የሚያስጥ ጥፋት በመፈፀማቸው በቀይ ካርድ ከጨዋታ ሜዳ የተወገደ ስለመሆኑ ሪፖርት ቀርቦበታል ።
ስለሆነም ተጫዋቹ ለፈፀመው ጥፋት በኢ.እ.ፌ ዲሲፕሊን መመሪያ ክፍል 2 ምዕራፍ 2 አንቀፅ 35(መ) መሰረት 1 ጨዋታ እንዲታገድ የየውድድርና ስነስርዓት ኮሚቴ ወስኗል።
3. አምሳሉ ጥላሁን (ፋሲል ከነማ): ከታች በተጠቀሱት ጨዋታዎች የቢጫ ማስጠንቅቂያ ካርድተመልክቷል።

- ማሰታውቂያ -
- ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርስቲ-ፋሲል ከነማ
- ፋሲል ከነማ-ሲዳማ ቡና
- ፋሲል ከነማ-ምድረ ገነት ሽረ
- መቻል-ፋሲል ከነማ
- ፋሲል ከነማ-ድሬደዋ ከተማ
ስለሆነም ተጫዋቹ ለፈፀመው ጥፋት በኢ.እ.ፌ ዲሲፕሊን መመሪያ መሰረት 1 ጨዋታ እንዲታገድ በተጨማሪ የገንዘብ ቅጣት ብር 15ዐዐ እንዲከፍል የውድድርና ስነስርዓት ኮሚቴ ወስኗል።
4. አርባምንጭ ከተማ : ክለቡ ከሸገር ከተማ ጋር ባደረገው የ6 ኛ ሳምንት እግርኳስ ጨዋታ የአርባምንጭ ከተማ ቡድን ተጫዋች የሆኑት
- ቡታቃ ሽመና
- ይገዙ ቦጋለ
- አካሉ እቲሞ
- ይሁን እንዳሻው
- ኤፍሬም ታምራት
- አካሉ አቲሞ
በተለያዩ ጥፋቶች ካርድ የተሰጣቸው በመሆኑ በኢ.እ.ፌ ዲሲፕሊን መመሪያ ክፍል 3 ምዕራፍ 3 አንቀፅ 65 (ሀ) መሰረት የገንዘብ ቅጣት ብር 5000 / አምስት ሺ/ እንዲከፍል የውድድርና ስነስርዓት ኮሚቴ ወስኗል፡፡
5. ሀዲያ ሆሳዕና : ክለቡ ከቅዱስ ጊዮርጊስ ጋር ባደረገው የ6 ኛ ሳምንት እግርኳስ ጨዋታ የሀዲያ ሆሳዕና ቡድን ተጫዋች የሆኑት
- ኢዮብ አለማየሁ
- አሸናፊ ኤልያስ
- ፀጋዓብ ግዛው
- ተመስገን ብርሃኑ
- ዳግም ንጉሴ
- ኦውሱ እንድሪውስ
በተለያዩ ጥፋቶች ካርድ የተሰጣቸው በመሆኑ በኢ.እ.ፌ ዲሲፕሊን መመሪያ ክፍል 3 ምዕራፍ 3 አንቀፅ 65 (ሀ) መሰረት የገንዘብ ቅጣት ብር 5000 / አምስት ሺ/ እንዲከፍል የውድድርና ስነስርዓት ኮሚቴ ወስኗል፡፡
6. ነገሌ አርሲ: ክለቡ ከአዳማ ከተማ ጋር ባደረገው የ6 ኛ ሳምንት እግርኳስ ጨዋታ የነገሌ አርሲ ቡድን ተጫዋች የሆኑት
- ዘሩባቤል ፈለቀ
- ሃቢብ ከማል
- ሮቦት ሰላሎ
- ዳዊት ተፈራ
- ገብረመስቀል ዱባለ
በተለያዩ ጥፋቶች ካርድ የተሰጣቸው በመሆኑ በኢ.እ.ፌ ዲሲፕሊን መመሪያ ክፍል 3 ምዕራፍ 3 አንቀፅ 65 (ሀ) መሰረት የገንዘብ ቅጣት ብር 5000 / አምስት ሺ/ እንዲከፍል የውድድርና ስነስርዓት ኮሚቴ ወስኗል፡፡
7. አርባ ምንጭ ከተማ ክለቡ ከ ሸገር ከተማ ጋር ባደረገው የ6ኛ ሳምንት እግር ኳስ ጨዋታ የክለቡ ግብ ጠባቂ አሰልጣኝ የዳኞች መልበሻ ክፍል በርን በቦክስ በመምታት ስለመስበሩ ሪፖርት ተደርጓል፡፡ ስለሆነም ክለቡ የተሰበረውን በር እንዲያሰራ ወይም የስታድየሙ ባለቤት አሰርቶ የሚያቀርበውን ዋጋ እንዲከፍል ወስኗል፡፡


