የካፍ ኮንፌዴሬሽን ዋንጫን አራት ኢትዮጵያዊያን ዳኞች ለመምራት ወደ አልጀርስ አምርተዋል።
በአፍሪካ እግር ኳስ ማህበር ካፍ አማካኝነት ከሚዘጋጁ የክለብ ውድድሮች መካከል ሁለተኛ ደረጃ ላይ የሚቀመጠው የካፍ ኮንፌዴሬሽን ዋንጫ የ2025/26 የውድድር ዘመን የምድብ የማጣሪያ ጨዋታዎች ከነገ ጀምሮ በየሀገራቱ መደረግ ይጀምራል። ከሚከናወኑ ጨዋታዎች መካከል የፊታችን ዕሁድ ህዳር 14 የአልጄሪያው ክለብ ዮ ኤስ ኤም አልጀርስ በሜዳው ከአይቮሪኮስቱ ዲ ሳን ፔድሮ ጋር ቀን 10፡00 ሰዓት በስታድ 5 ጁሌት 1962 ስታዲየም ሲገናኙ አራት ኢትዮጵያዊያን አለም አቀፍ ዳኞች እንዲመሩ ስለመመረጣቸው ሀትሪክ ስፖርት አረጋግጣለች።
ጨዋታውን በመሐል ዳኝነት ቴዎድሮስ ምትኩ በረዳትነት ትግል ግዛው እና ፋሲካ የኋላሸት በአራተኛ ዳኝነት ደግሞ በላይ ታደሠ የሚመሩት ይሆናል።



