ፀጋዬ ኪዳነማሪያም ወደ ወላይታ ድቻ አምርቷል

በዘንድሮው የቤትኪንግ ፕሪምየር ሊግ ከግማሽ የውድድር ዓመት በኋላ በመምጣት እስከ ሊጉ ማብቂያ ድረስ በሀላፊነት የመራው አሰልጣኝ ፀጋዬ ኪዳነማርያም ጅማ አባጅፋርን በመለቀቅ ወላይታ ድቻን ለማሰልጠን መስማማቱ ታውቋል።

በሊጉ 8ተኛ ደረጃን በመያዝ ያጠናቀቀው ወላይታ ድቻ አሰልጣኙን ዘላለም ሽፈራውን ለማቆየት ያደረገው ጥረት ባለመሳካቱ ጅማ አባጅፋርን ከመውረድ ያልታደጉትን አሰልጣኝ ፀጋዬ ኪዳነማርያምን በአንድ ዓመት ውል ማስፈረም ችሏል።

በእግር ኳስ ተጨዋችነት ዘመኑ ለእህል ንግድ እና ለታክሲ ቡድን ለመጫወት የቻለውና ወደ አሰልጣኝነት ካመራ በኋላ  ለትራንስ ኢትዮጵያንና ለኢትዮጵያ ታዳጊ ብሄራዊ ቡድንን በረዳት አሰልጣኝነት ሲመራ  ሐረር ቢራን ፤ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክን፣ ኢትዮጵያ ቡናን፣ አርባምንጭ ከተማን ፤ ወልዋሎ አዲግራት.ዮ እና ጅማ አባጅፋርን በዋና አሰልጣኝነት ማሰልጠን ችሏል።

hatricksport team

Hatricksport team

Facebook

hatricksport team

Hatricksport team