በ2014 ቤትኪንግ ፕሪሚየር ሊግ በትግራይ ክለቦች ዙሪያ ፌዴሬሽኑ ውሳኔ አሳልፏል

የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ከዚህ ቀደም የትግራይ ክልል ክለቦች የ2013ዓ.ም የውድድር ተሳትፎን በተመለከተ ውሳኔ ማስተላለፋ ይታወሳል ። በውሳኔውም በ2013 ዓ.ም በተለያዩ የሊግ ደረጃዎች በሚካሄዱ ውድድሮች መሳተፍ ያልቻሉ የትግራይ ክልል ክለቦች ለ2014 ብቻ በነበሩበት ሊግ እንዲሳተፉ እና እንዲጠበቁ መወሰኑ ይታወቃል።

ይሁን እና የ2013ዓ.ም የውድድር ዘመን እየተጠናቀቀ ባለበት ሰዓት የተለያዩ የፍላጎት ውዝግቦች በመደመጥ ላይ ይገኛሉ። በተለይ የፕሪምየር ሊግ ውድድር ላይ የክለቦች መውጣት እና መውረድን ተከትሎ የተሳሳተ መረጃ በመሰራጨቱ የእግር ኳስ ቤተሰቡ ክለቦችን ጨምሮ በአሁን ሰዓት ግራ በመጋባት ላይ ይገኛሉ።

ቀደም ሲል የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ሼር ካምፓኒ ያቀረበው ሐሳብም በግብዓትነት የሚታይ እንጂ ውሳኔ አለመሆኑን እየገለጽን፤ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የእግር ኳሱ የበላይ አስተዳዳሪ እንደመሆኑ መጠን በዚህ ጉዳይ ላይ ስልጣን እና ኃላፊነት ያለው የፌዴሬሽኑ የስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ በመሆኑ በቀጣይ ከትግራይ ክልል ክለቦች ጋር የተጀመሩ ስራዎች እንደተጠናቀቁ የክለቦች የመውጣት እና የመውረድ ውሳኔዎችን የምናሳውቅ መሆኑን እንገልጻለን።

Via-eff

hatricksport team

Hatricksport team

Facebook

hatricksport team

Hatricksport team