አዲስ ግደይ በዛሬው እለት ቀዶ ጥገና አከናወነ

በ2013 ዓ.ም ፈረሰኞቹን የተቀላቀለው የቀድሞው የሲዳማ ቡና የፊት መስመር አጥቂ አዲስ ግደይ በዛሬው እለት የጉልበት ቀዶ ጥገና በማርሻል ከፍተኛ የቀዶ ጥገና ማዕከል አድርጓል፡፡

ፈረሰኞቹ ደብረዘይት በሚገኘው በክቡር አቶ ይድነቃቸው ተሰማ የታዳጊዎች ማዕከል ከሲዳማ ቡና ጋር በነበራቸው የወዳጅነት ጨዋታ ላይ ተሰላፊ የነበረው የክለባችን አጥቂ አዲስ ግደይ፣ በሰዓቱ የጉልባት ጉዳት ACL( Anterior cruciate ligament) እና meniscus ተብሎ በህክምና የሚጠራውን ጉዳት አስተናግዶ ለረጅም ጊዜ ከሜዳ መራቁ ይታወሳል፡፡ በመሆኑም አዲስ ግደይ በዛሬው እለት ከጠዋቱ 2፡30- 7፡30 የፈጀ ቀዶ ጥገና በጥሩ ሁኔታ አከናውኗል፡፡
አዲስ ሙሉ በሙሉ ከህመሙ አገግሞ ወደ ሜዳ ለመመለስ ከ ስድስት እስከ ዘጠኝ ወር ሊፈጅበት እንደሚችልም የህክምና ባለሙያዎች ገልጸዋል፡፡

Via – Saint George S.A

hatricksport team

Hatricksport team

Facebook

hatricksport team

Hatricksport team