” የሞባይል ካርድ የምንሞላበት ገንዘብ እንኳን የለንም ” የጅማ አባ ጅፋር ተጫዋቾች ቅሬታ

በዘንድሮው የውድድር ዓመት የቤት ኪንግ ኢትዮጵያ ፕርሚየር ሊግ የትግራይ ሶስቱ ክለቦች መሳተፋቸው እውን ከሆነ መውረዳቸውን ያረጋገጡት የጅማ አባ ጅፋር እግር ኳስ ክለብ ተጫዋቾች ቅሬታ አሁንም ቀጥሏል ።

በውድድር ዓመቱ መጀመሪያ ተጫዋቾች የምንበላው አጣን ከማለት የጀመረው የክለቡ ቅሬታ በአክስዮን ማህበሩ የ ስምንት ሚልዮን ብር ገንዘብ ባገኙ ማግስትም ቀጥሏል ።

ለሀትሪክ ስፖርት ቅሬታቸውን ያሰሙ የክለቡ ተጫዋቾች እንደገለፁት የተለያዩ ቅሬታዎቻቸውን አሰምተዋል ።

” ሀዋሳ ላይ የነበረው ውድድር እንደተጠናቀቀ ወደ ጅማ ካቀናን በኋላ ሁሉም ነገር እዛ እንደሚፈታ ቃል ቢገባልንም እስከ አሁን ምንም የተለወጠ ነገር የለም ” የጅማ አባ ጅፋር ተጫዋች

ሀትሪክ ስፖርት ከውስጥ ምንጮች ለማወቅ እንደቻለችው በተለይም በክለቡ ውስጥ የሚገኙ የውጭ ሀገር ተጫዋቾች በከፍተኛ ችግር ላይ እንደሚገኙ ለመታዘብ ችለናል ።

” ታመን የሚያሳክመን የለም ፣ እንዳንታከም እጃችን ላይ ገንዘብ የለም ፣ ወደ ሀገራችን ለመሄድ ብንፈልገም እስከ አሁን እዚህ እንገኛለን ” የጅማ አባ ጅፋር ተጫዋች

ሀትሪክ ከ ሌላኛ የ ክለቡ ተጫዋች ጋር ቆይታን ስታደርግ ” በክለቡ የሚገኙ የውጭ ሀገር ተጫቾች በከፍተኛ የ ገንዘብ ችግር ውስጥ ይገኛሉ ፣ የሞባይል ካርድ የሚሞሉበት አጥተው እኛ እየላክንላቸው እንገኛለን ” ሲል አስተያየቱን ሰጥቶናል ።

ሀትሪክ ስፖርት የተጫዋቾቹን ቅሬታ በመያዝ የክለቡ ከፍተኛ ሀላፊዎች ጋር ስልክ ብንደውልም አቶ ሱልጣን ( ስልካቸው ዝግ ) ፣ አቶ ናስር ( ስላከቸው ዝግ ) ፣ የቡድኑ መሪ አቶ ጅሀድ ከድር ስልካቸው ባለመነሳቱ ምክንያት የክለቡን አቋም ብሎም ምላሽ ለማግኘት ተቸግረናል ።

ሀትሪክ ስፖርት የክለቡን ከፍተኛ ሀላፊዎች ማግኘት በተቻለበት ሰዓት በማነጋገር ምላሹን ተከታትለን የምናቀርብ ይሆናል ።

Hatricksport website Editor

Twitter

kidus Yoftahe

Hatricksport website Editor