የዋልያዎቹ አሰልጣኝ ውበቱ አባተ አስተያየት

 

የዋልያዎቹ አሰልጣኝ ውበቱ አባተ በአሁን ሰዓት የትላንትናውን ድል ተከትሎ አስተያየታቸውን በመስጠት ላይ ይገኛሉ ።
በጋዜጣዊ መግለጫው ላይ የዋልያዎቹ አምበል አስቻለው ታመነ ባጋጠመው የጡንቻ መሸማቀቅ ጉዳት ዘግየት ብሎ መግለጫ ላይ ሊገኝ ችሏል ።

የተነሱ ዋና ነጥቦች :-

– በምንፈልገው ልክ የደጋፊ ድጋፍ ባለመኖሩ የትላንትንቱን ጨዋታ ከሜዳ ውጪ እንዳደረግን ነው የምንቆጥረው ያሰብነውን በማሳካታችን ደስ ብሎኛል ።

– ብሔራዊብሔራዊ ቡድኑ ባለፉት አንድ ዓመታት የነበረበት የቴክኒካል መረጃ በፅሁፍ ብጠይቅም ያቀረበልኝ አካል አልነበረም ።

– አማኑኤል ገ/ሚካኤል ያስቆጠራትን የመጀመሪያውን ጎል ባርሴሎና ቢያስቆጥረው ኖሮ የአለም ህዝብ ያጨበጭብላቸው እንዲሁም የሚዲያው ማድመቂያ ይሆን ነበር ፣ ንፉግ መሆን ጥሩ አይደለም ።

– ለአፍሪካ ዋንጫ የማለፍ ዕድሉ አሁንም በእኛው ውጤት ላይ የተንጠለጠለ ነው ።

– ከማዳጋስጋሩ ጨዋታ አስቀድሞ በትንሹ አንድ የወዳጅነት ጨዋታን ማግኘት እንዳለብን ከፌዴሬሽኑ ጋር ተነጋግረናል ።

– አንደኛ በሆንኩበት ቡድን ተባርሬ አውቃለሁ አንድም ቀን ግን ስራ አጥቼ አላውቅም ፣ አሁንም ቢሆን አሸንፈን እንጂ ለአፍሪካ ዋንጫ አላለፍንም ።

የአስቻለው ታመነ አስተያየት !

– የኒያሚው ጨዋታ ውጤቱን የሚገልፅ አልነበረው ወደ ብሔራዊ ቡድን ከመጣሁነት ጊዜ ጀምሮ እንዲህ ተጫውተን አናቅም ።

– ከኒያሚው ጨዋታ በኋላ በማህበራዊ ድህረ ገፅ ላይ ይሰጡ የነበሩ ትችቶች በጣም ያሙ ነበር ። ብሔራዊ ቡድን ሀገር ማለት እስከ ሆነ ድረስ ውጤት ሲመጣ ብቻ ሳይሆን ሲጣፈም የህዝቡ ድጋፍ ያስፈልገናል ።

– ሁላችንም በማሸነፍ ሀገር አንድ የማድረግ አላምን አንግበን ነበር በፌዴረለሽኑ ገፅ ላይ ስንሰጥ የነበረው አስተያየቶች ከዚህ ተነስተን ነበር ።

– ደጋፊው ገብቶ ቢሆን ኖሮ ደስ ይለን ነበር ሆኖም ግን ተፅዕኖ አልፈጠረብንም ።

– በእኔ እና በ ያሬድ ባየህ በኩል ምንም አይነት ግጭት የለም ፣ ከማንም ጋር ብጫወት ደስ ይለኛል ሁሉም በችሎታ ነው የመጣው እንጂ በዘመድ አልመጣም ፣ ከያሬድ ጋር ተጣልተዋል ተብሎ ነበር በሰዓቱ ተሰምቶን ነበር ፣ እኔ እና ያሬድ በክፉ አይን እንኳን ተያይተን አናቅም ።

Hatricksport website Editor

Twitter

kidus Yoftahe

Hatricksport website Editor