ስድስት ተጨዋቾች ከመቐለ አዲስ አበባ ገቡ!

 

*..የመቀለ 70 እንደርታ አመራሮች አያውቁም

በሀገር መከላከያ ሰራዊት ህግ የማስከበር ዘመቻ ምክንያት ጦርነት ውስጥ ያለችው መቐለ ለእግርኳስ ተጨዋቾች የምትመች ባትሆንም የመቐለ 70 እንደርታ ተጨዋቾች ግን በቀን ሁለቴ ልምምድ ሲሰሩ ሰንብተዋል እስከ ሰኞ ጠዋት ድረስ…. በተለምዶ ባሎኒ ሜዳ ከሚገኘው የማዘጋጃ ቤት ቢሮ አጠገብ የሚገኘው የቅዱስ ጊዮርጊስ ገዳም ውስጥ ያለውን አንደር ግራውንዱን ተፈላጊዎቹ የህወሀት ሰዎች ለስብሰባነት ለመጠቀም የገዳሙን አባቶችና አገልጋዮች በማስወጣት መሠብሠብ መጀመራቸውን የመከላከያ ሃይሉ መረጃ አግኝቶ በድሮን ጥቃት መሠንዘሩ ታውቋል፡፡

ይህን ተከትሎ የደህንነት ስሜት ያልተሰማቸው 6 የመቀለ 70 ተጨዋቾች ሰኞ ምሽት ተነስተው በሰመራ አፋር አድርገው ዛሬ ጠዋት አዲስ አበባ መግባታቸውን ከታማኝ ምንጭ የተገኘው መረጃ ያስረዳል፡፡ እነሱም አራ ቱ አፍሪካዊያን ኦኪኪ አፎላቢ… ዳንኤል ኦጄ..ሲሶኮና ካሉሺያ እንዲሁም ስዩም ተስፋዬና አሚን ነስሩ መሆናቸውም ታውቋል፡፡ ተጨዋቾቹ የክለቡ አመራሮች በተለይ ፕሬዝዳንቱ አቶ ሽፈራው ጋር ለመገናኘት ሞክረው አለመሳካቱ ታውቋል፡፡ ተጨዋቾቹ ከመቀለ ሲነሱም ሆነ አዲስ አበባ መግባታቸውን የክለቡ አመራሮች መረጃው የሌላቸው ሲሆን ለሻምፒየንስ ሊጉ ዝግጅት ሲባል በቀጣይ ጥቂት ቀናቶች ሌሎቹ ተጨዋቾች አዲስ አበባ ለዝግጅት እንዲመጡ ለማድረግ እየተሰራ መሆኑን ምንጫችን ገልጿል፡፡

በቀጣይም የወልዋሎ አዲግራትና የስሁል ሽረ አባላትን ወደ አዲስ አበባ ለዝግጅት ለማምጣት ሙከራዎቹ ተጠናክረው ቀጥለዋል፡፡

Editor at Hatricksport

Facebook

ዮሴፍ ከፈለኝ

Editor at Hatricksport