ጀማል ጣሰው ለዋሊያዎቹ ተጠርቷል

 

ለኒጀሩ ጨዋታ ዝግጅት ከተጠሩት 5 ግብ ጠባቂዎች ውጪ የነበረው ጀማል ጣሰው 6ኛ ሆኖ ተጠርቷል፡፡

አሰልጣኝ ውበቱም ለፌዴሬሽኑ አሳውቀዋል፡፡ ለዝግጅት ከተጠሩት ተጨዋቾች መሃል ኢኳቶሪያል ጊኒ ለሚገኝ ክለብ ሙከራ ላይ ያለው መስፍን ጣሰውና ለግብጹ ምስር አልማቃሳ የሚጫወተው ሽመልስ በቀለ ለውድድር እንጂ ለዝግጅት ላይደርሱ ይችላሉ በመባሉ ዝግጅቱ በ38 ተጨዋቾች መሃል የሚካሄድ መሆኑ ታውቋል፡፡ የቡድኑ አባላት ከነገ በስቲያ ቅዳሜ ፌዴሬሽን ጽ/ቤት ሪፖርት ካደረጉ በኋላ ዝግጅቱን ሰኞ ይጀምራሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡

Editor at Hatricksport

Facebook

ዮሴፍ ከፈለኝ

Editor at Hatricksport