በአሰልጣኝ ውበቱ አባተ ጥሪ ከቀረበላቸው ተጫዋቾች መካከል አንዱ የሆነው የመስመር ተጫዋች ሚኪያስ መኮንን ጉዳት ማስተናገዱን አሰልጣኝ ውበቱ አባተ በጋዜጣዊ መግለጫቸው ከደቂቃዎች በፊት አሳውቀዋል ።
ሚኪያስ መኮንን ከ ዛምቢያው የዛሬ የአቋም መፈተሻ አስቀድሞ ረፋድ ላይ በነበራቸው የልምምድ ጊዜ የጡንቻ መሸማቀቀ ጉዳት እንዳስተናገደ አሰልጣኝ ውበቱ አባተ ገልፀዋል ።
ከሚኪያስ መኮንን በተጨማሪ ከቀናት በፊት ሐሙስ የቡናማዎቹ የፊት መስመር አጥቂ አቡበከር ነስሩ ተመሳሳይ ጉዳት ማስተናገዱን ለማወቅ ተችሏል ።
- ማሰታውቂያ -
ከሁለቱ ተጫዋቾች በተጨማሪም የቅዱስ ጊዮርጊሱ የፊት መስመር አጥቂ አቤል ያለው ጉዳት ማስተናገዱ ተሰምቷል ።