የቅዱስ ጊዮርጊሱ አጥቂ አቤል ያለው ከዋሊያዎቹ ስብስብ ውስጥ ያልተካተተው በጉዳት መሆኑ ተነገረ።
ተጨዋቹ ተመርጠው ለወዳጅነት ጨዋታ ዝግጁ ከሆኑት 23 ተጨዋቾችም ይሁን ከተቀነሱት 6 ተጨዋቾች ውስጥ አለመካተቱን ተከትሎ የስፖርት ቤተሰቡ የአቤል ያለው ጉዳይ ምንድነው እያለ ሲጠይቅ ከሰሞኑ ሰንብቷል።
ከፌዴሬሽኑ በተገኘ መረጃ ግን ቅዱስ ጊዮርጊስ የአቤል ያለው ጉዳት ላይ መሆኑን በመግለጽ የሀኪም ማስረጃ በማቅረቡ ተጨዋቹ ከኮሞሮስ ጋር ለሚደረገው የወዳጅነት ጨዋታ እየተዘጋጁ ካሉት የዋሊያዎቹ ስብስብ ውጪ መደረጉ ታውቋል።
ዋሊያዎቹ የፊታችን ዓርብ መጋቢት 16/2014 ከኮሞሮስ ብሄራዊ ቡድን ጋር የወዳጅነት ጨዋታ የሚያደርጉ ሲሆን ከነገ በስቲያ ረቡዕ ጠዋት ወደስፍራው ያቀናሉ ተብሎ ይጠበቃል።
አስተያየት ይስጡ