” ዋልያዎቹ በካሜሩኑ የአፍሪካ ዋንጫ ከተሳታፊነት በዘለለ ጠንካራ ተፎካካሪ እንደሚሆኑ እተማመናለው ” ሰርጆቪች ሚሉቲን ሚቾ

በፈረሰኞቹ ቤት በነበራቸው ቆይታ ስኬታማ በሚባል ጊዜያቸው የሚታወሱት እና በሁሉም የስፖርት አፍቃሪያን ዘንድ ተወዳጅ የሆኑት ሰርቢያዊው አሰልጣኝ ሰርጆቪች ሚሉቲን ሚቾ የዋልያዎቹን ወደ አፍሪካ ዋንጫ መመለስ ተከትሎ የእንኳን ደስ ያላችሁ መልዕክታቸውን ለሀትሪክ ስፖርት አድርሰዋል ።

” የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ለአፍሪካ ዋንጫው በማለፉ ከልቤ የተሰማኝን ደስታ ልገልፅ እፈልጋለው ። የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ዋልያዎቹ ማለፉን ተከትሎ ለመላው የኢትዮጵያ ህዝብ ፣ የፌዴሬሽኑ አመራሮች ፣ ለጓደኛዬ አቶ ኢሳያስ ፣ ለአሰልጣኝ ውበቱ ፣ ለመላው የአሰልጣኞች ክፍል እንዲሁም ለታላላቆቹ ተጫዋቾች ይህ ውጤት እንዲመጣ በሜዳ ላይ ከፍተኛ ተጋድሎ ላደረጉት ሁሉ ከፍተኛዬ ምስጋናዬን ላቀርብላቸው እወዳለው ።

ሁሉም ከላይ የተጠቀሱት አካላት ጨምሮ የእግር ኳስ ቤተሰቡ ለኢትዮጵያ ያለኝን ፍቅር እንዲሁም ስለ ኢትዮጵያ ምን እንደማስብ ያቃል ፣ የ ኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በካሜሩኑ የአፍሪካ ዋንጫ ከተሳታፊነት በዘለለ ጠንካራ ተፎካካሪ ሆነው እንደሚቀርቡ እተማመናለው ። ይህ ግን እንዲሆን ከአሁኑ ጥሩ ዝግጅትን ማድረግ ይገባችዋል “።

በመጨረሻም አሰልጣኝ ሚቾ አስተያየታቸውን ሲቋጩ ” አግዚአብሔር ይመስገን እንኳን ደስ አላችሁ ፣ እግዚአብሔር ይርዳችሁ ፣ ኢትዮጵያ ሀገሬ ፣ በጣም አመሰግናለው ” ሲሉ ከሀትሪክ ስፖርት ጋር የነበራቸውን ቆይታ አገባደዋል

Hatricksport website Editor

Twitter

kidus Yoftahe

Hatricksport website Editor