የኢትዮጵያ እና የሱዳን የአቋም መፈተሻ ጨዋታ !

 

ዋልያዎቹ ከፊታችን ለሚጠብቃቸው የአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ ከ ኒጀር ጋር ለሚያደርጉት የደርሶ መልስ ጨዋታ ጠንከር ያለ ልምምዳቸውን ማደረግ ቀጥለዋል ።

ለዚህም ጨዋታ ይረዳቸው ዘንድ በመጪው አርብ ከ ሱዳን ብሔራዊ ቡድን ጋር የአቋም መፈተሻ ጨዋታ ለማድረግ ከስምምነት ላይ መድረሳቸውን ታውቋል ።

ሀትሪክ ስፖርት የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የህዝብ ግንኙነት ሀላፊን አቶ ባህሩ ጥላሁንን በጉዳዩ ዙሪያ አነጋግራ ሁለቱ ሀገራት የወዳጅነት ጨዋታ ለማካሄድ በኢሜል በተደረገ ግንኙነት መስማማታቸውን ሲገልፁልን ይፋዊ የሆነ ፈቃድን እየጠበቁ እንደሚገኙ ገልፀውልናል ።

Hatricksport website Editor

Twitter

kidus Yoftahe

Hatricksport website Editor