ዋልያዎቹ ልምምዳቸው ከ ካፍ አካዳሚ ውጪ አደረጉ !

 

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ዋልያዎቹ ያለፉት ሳምንታት በካፍ አካዳሚ የልህቀት ማዕከል መቀመጫቸውን በማድረግ ልምምዳቸውን ሲሰሩ ሲቆዩ ለመጀመሪያ ጊዜ የዛሬውን የረፋድ ልምምዳቸውን በአዲስ አበባ ስታዲየም ማድጋቸው ለማወቅ ተችሏል ።

በዛሬው ዕለት የአዲስ አበባ ስታዲየም ልምምዳቸው የእርስ በእርስ ጨዋታዎችን ለማድረግ ችለዋል ።

በዛሬው የልምምድ መርሐ ግብር ላይ ከዚህ ቀደም መጠነኛ ጉዳት አስተናግዶ የቆየው የፊት መስመር አጥቂው አቡበክር ነስሩ ቡድኑን በመቀላቀል ልምምድ መስራት ጀምሯል ።

ከቀናት በፊት ጉዳት ያስተናገደው ሙጂብ ቃሲም እንዲሁም አማኑኤል ዮሐንስ ለብቻቸው ልምምድ መስራታቸውን ለማወቅ ተችሏል ።

hatricksport team

Hatricksport team

Facebook

hatricksport team

Hatricksport team