ዋልያዎቹ የመጨረሻ ልምምዳቸውን አድርገዋል !

 

በመጪው ሳምንት አርብ ለሚጠብቃቸው ወሳኝ የአፍሪካ ዋንጫ መርሀ ግብር በነገው ዕለት ወደ ስፍራው እንደሚያቀኑ የሚጠበቁት ዋልያዎቹ ዛሬ ረፋድ ላይ ልምምዳቸውን መስራት ችለዋል ።

በዛሬው ልምምድ ላይ ሙሉ የቡድኑ አባላት በሙሉ ጤንነት ላይ ተገኝተው ልምምዳቸውም ሲሰሩ ሙጂብ ቃሲም እና ሱራፌል ዳኛቸው ለብቻቸው ቀለል ያለ ልምምዶችን ለመስራት እንደቻሉ ለማወቅ ተችሏል ።

 

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ወደ ኒጀር የማያቀኑ ሶስት ተጫዋቾችን በዛሬው ዕለት እንደሚያሳውቁ ሲጠበቅ በትላንትናው ዕለት የተደረገላቸው የኮሮና ቫይረስ ምርመራ አመሻሹን ይገለፃል ተብሎ ይጠበቃል ።

Hatricksport website Editor

Twitter

kidus Yoftahe

Hatricksport website Editor