ኢትዮ.ኤሌክትሪክ 7 አሰልጣኞችን ለማክሰኞ ቀጥሯል

 

ኢትዮ ኤሌክትሪክ ባወጣው የዋናው ቡድን የአሰልጣኝነት የቅጥር ማስታወቂያ ከተወዳደሩ 34 አሰልጣኞች መሃል የተዋቀረው ኮሚቴ ሰባቱን መርጦ ለቃለ ምልልስ ማክሰኞ ጠዋት ቀጠሮ መስጠቱ ታውቋል፡፡

በክለቡ ዋና ስራአስኪያጅ አቶ ለማ ደበሌ የወጣው ማስታወቂያ እንደሚያሳየው አሰልጣኝ ብርሃኔ ገ/እግዚአብሄር አሰልጣኝ ጥላሁን መንገሻ አሰልጣኝ ክፍሌ ቦልተና አሰልጣኝ ግርማ ሃ/ዮሃንስ አሰልጣኝ ጳውሎስ ጌታቸው አሰልጣኝ ተገኔ ነጋሽና አሰልጣኝ ሰብስቤ ይባስን ለመጨረሻውና ወሳኙ ኢንተርቪው ቀጠሮ መስጠቱ ታውቋል፡፡

አሸናፊው አሰልጣኝ ኢትዮ ኤሌክትሪክን ወደ ፕሪሚየር ሊግ የማሳለፍ ሃላፊነት የሚጣልበት ይሆናል፡፡ ከዚህ የአሰልጣኞች ቅጥር አሁን ድረስ ምንም አይነት እንቅስቃሴ እየተደረገበት የሌለውና ቀጣይ መጻኢ ዕድሉ አነጋጋሪ የሆነው የሰበታ ከተማ ጉዳይ አነጋጋሪ ሆኗል፡፡

Editor at Hatricksport

Facebook

ዮሴፍ ከፈለኝ

Editor at Hatricksport