” ተጨዋቾች የአሰልጣኝ ብርሃኑም ሆነ የኔ አይደሉም የኢትዮጵያ ናቸው ተናበን መስራት የግድ ነው”
“ሴቶችንና አገሪቷን አክብራችሁ ስለመጣችሁ አመሰግናለሁ”
አሰልጣኝ ፍሬው ሃ/ገብርኤል
የ20 አመት ሴቶች ብ/ቡድን አሰልጣኝ
20 አመት ሴቶች ብሄራዊ ቡድን ለኮስታሪካ የአለም ዋንጫ ለማለፍ ከሩዋንዳ ጋር ላለው ጨዋታ ነገ ጠዋት ወደ ኪጋሊ ያቀናሉ።
የቡድኑ ዋና አሰልጣኝ ፍሬው ሃይለ ገብርኤል በፌዴሬሽኑ ጽ/ቤት በሰጡት መግለጫ ለ22 ቀናት ልምምድ ማድረጋቸውና ወደ 40 ተጨዋቾች ይዘው ሲሰሩ እንደነበር ገልጸዋል።”
ከውድድር ላይ በመጡ ጊዜ ለቡሩንዲ ጨዋታ የሰራነው ልምምድ ከ15 ቀን የማይበልጥ በመሆኑ የአሁኑ ይሻላል የአሁኑ ጊዜው 22 ቀን ቢሆንም ከውድድር ስላልመጡ ትግል ነበረው” ሲሉ ተናግረዋል። አሰልጣኙ “40 ተጨዋቾች መርጠው ልምምድ ከሰሩ በኋላ ሁለት ተጨዋቾች በግል 3 ተጨዋቾቾ በጉዳት፣ 7 ተጨዋቾች በአቋም መውረድ የተቀነሱ ሲሆን ወደ ሩዋንዳ ከመጓዛችን በፊት ሌሎች 7 ተጨዋቾችን እንቀንሳለን” ሲሉ አስረድተዋል።
አሰልጣኙ የሩዋንዳ ቡድንን በተመለከተ “ባለፉት ሁለት አመታት ምንም አይነት ጨዋታ ስላልነበር ስለ ሩዋንዳ ምንም መረጃ የለኝም ስለዚህ የአሰልጣኝ ልዩነት ብዬ በማስበው የግጥሚያው ቀን ግጥሚያውን አይቼና አንብቤ ለማሸነፍ የማደርገው ጥረት ነው”ሲሉ አስረድተዋል።
ከሉሲዎቹ አሰልጣኝ ብርሃኑ ግዛው ጋር ትናበባላችሁ ወይ የተባሉት አሰልጣኝ ፍሬው” ባለፉት አመታት ውድድር ስላልነበር መናበብ አልቻልንም ለቀጣዩ ግን በግሌ ዝግጁ ነኝ ተጨዋቾች
የአሰልጣኝ ብርሃኑ ወይም የኔ አይደሉም የኢትዮጵያ ናቸው ተናበን መስራት የግድ ነው”ሲሉ መልሰዋል። መግለጫው ላይ ለተገኙት ቁጥራቸው ላነሰ ጋዜጠኞች “ሴቶችንና አገሪቷን አክብራችሁ ስለመጣችሁ አመሰግናለሁ” ያሉት አሰልጣኙ ” ስለዝግጅቴ መሟላት አለመሟላት ምንም ማለት አልሻም በተቻለ መጠን የችግር ሳይሆን የመፍትሄ አካል መሆን ነው የምፈልገው”ሲሉ ተናግረዋል።
አስተያየት ይስጡ