..የሰበሮምና ሞውሪንሆ ጥምረት….
ከቅዱስ ጊዮርጊስ ጋር የአንድ አመት ውል ቢኖረውም ክለቡ ብሩን መልሶ እንዲለቅ የወሰነበት ጌታነህ ከበደ ከሰበታ ከተማ ጋር ተስማምቷል።
ከታማኝ ምንጭ በተገኘ መረጃ ጌታነህ ከበደ ሲዲማ ቡና ጋር ቢደራደርም ባለመስማማቱና ሰበታ ከተማዎች ጋር ያደረገው ውይይት በመግባባት መጠናቀቁ ተጨዋቹን በደቡብ ፖሊስ የመጀመሪያ አሰልጣኙ ዘላለም ሽፈራው /ሞውሪንሆ/ ስር የመሰልጠን እድል እንዲያገኝ ረድቶታል።
ባለፈው ሳምንት ሀዋሳ ላይ ከሰበታ ከተማዎች ጋር ልምምድ መስራቱ ለድርድሩ በር መክፈቱ ይነገራል። ሁለቱ ወገኖች በደመወዝና በጥቅማ ጥቅም ዙሪያ የተስማሙ ሲሆን ከፈረሰኞቹ ጋር በሚመልሰው ገንዘብ ዙሪያ የመጨረሻ ውይይት አድርጎና ክፍያውን ከፈጸመ በኋላ ሰበታዎችን ይቀላቀላል ተብሎ ይጠበቃል።
ሰበታ ከተማዎች የሚጠበቅባቸውን ለማድረግ ቁርጠኛ አቋም መያዛቸው ታውቋል።
አስተያየት ይስጡ