ቅዱስ ጊዮርጊስ እና የኢትዮጵያ ከ 20 ዓመት ብሔራዊ ቡድን ጨዋታቸውን አካሄዱ !

በዛሬው ዕለት ረፋዱን ከቀናት በፊት በተያዘ ቀነ ቀጠሮ የሁለቱ መርሐ ግብር ሲካሄድ ጨዋታው ያለ ምንም ግብ አቻ ለመውጣት ችለዋል ፡፡
የኢትዮጵያ ከ 20 ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድን በ አሰልጣኝ ተመስገን ዳና በዛሬው ጨዋታ ሁለት ቡድኖች ይዘው ሲቀርቡ ከፊታችን ለሚጠብቃቸው የሴካፋ አልፎም ለአፍሪካ ዋንጫ ለማለፍ በሚካሄደው የውድድር መድረክ ላይ ቡድናቸውን አይተውበታል ተብሎ ይጠበቃል ፡፡

ብሔራዊ ቡድኑ ለ ሰላሳ ተጫዋቾች ጥሪ አቅርበው ልምምዳቸውን አጠናክረው ሲቀጥሉ በነገው ዕለትም በአዲስ አበባ ስታዲየም ተመሳሳይ የልምምድ መርሐ ግብራቸውን የሚቀጥሉ ይሆናል ፡፡
የፈረሰኞቹ አሰልጣኝ ቡድኑን ከተረከቡ በኋላ የመጀመሪያ ጨዋታቸውን ማካሄድ ሲችሉ በዝውውር መስኮቱ ቡድኑን መቀላቀል የቻለው አዲስ ግደይ የመጀመሪያ ጨዋታውን ማድረጉን ለማወቅ ተችሏል ፡፡

ኤርነስት ሚደንድሮፕ በዛሬው ጨዋታ ላይ ፓትሪክ ማታሲ ፤ አብድልከሪም መሐመድ ፤ ሄኖክ አዱኛ ፤ ምንተስኖት አዳነ ፤ ፍሪምፖንግ ሜንሱ ፤ ሙሉዓለም መስፍን ፤ ደስታ ደሙ ፤ ያብስራ ተስፋዬ ፤ አዲስ ግደይ ፤ ፀጋዬ ፤ አቤል ያለው በመጀመሪያ አሳላለፍ ውስጥ መካተታቸውን ለማወቅ ተችሏል ፡፡

ተመስገን ዳና ከጨዋታው መጠናቀቅ በኋላ ከ ሀትሪክ ስፖርት ጋር ቆይታን ሲያደርግ የቅዱስ ጊዮርጊስ ስፖርት ክለብን ሲያመሰግኑ በሀለቱም አጋማሾች የተለያዩ ተጫዋቾችን መሞከራቸውን ገልፀውልናል ፡፡

Hatricksport website Editor

Twitter

kidus Yoftahe

Hatricksport website Editor