ኢንስትራክተር አብርሃም መብራቱ ወደ ሰበታ ከተማ አቀና

 

*…አሰልጣኝ አብርሃም መብራቱና አሰልጣኝ ውበቱ አባተ
ቦታ ተቀያየሩ

* ሰበታዎች የአሰልጣኙን ዕረፍት አቋርጠዋል

 

የሰበታ ከተማ እግርኳስ ክለብ አመራሮች አሰልጣኝ ውበቱ አባተን ወደ ዋሊያዎቹ ከሸኙ በኋላ ሁነኛ አሰልጣኝ ሲያፈላልጉ ቆይተዋል ባወጡት የአሰልጣኝ ቅጥር ማስታወቂያም ልባቸው አልረካም..ነገር ግን አንድ ሰው ላይ ትኩረት አድርገዋል .ኢንስትራክተር አብርሃም መብራቱ ላይ…
ተደጋጋሚ ሙከራቸው ግቡን መቶላቸዋል፡፡ዕረፍት እፈልጋለሁ ያለው አሰልጣኝ አብርሃም ከተደጋጋሚ ሙከራ በኋላ ለሰበታ ከተማ አመራሮች እጁን ሰጥቶ የአሰልጣኝ ውበቱን ስብስብን ለመረከብ መስማማቱን ከታማኝ ምንጭ የተገኘው መረጃ ያስረዳል፡፡ አጭሩ የኢንስትራክተር አብርሃም ዕረፍት ተቋርጦ ወደስራው ተመልሷል፡፡ የሁለቱ ወገኖች ስምምነት በቅርብ ጊዜ ውስጥ ይፋ ይደረጋል ተብሎ ይጠበቃል

Editor at Hatricksport

Facebook

ዮሴፍ ከፈለኝ

Editor at Hatricksport