አሰልጣኝ ክፍሌ ቦልተና የተስማማሁት ከኢትዮ ኤሌክትሪክ ጋር ነው አለ

አሰልጣኝ ክፍሌ ቦልተና
የተስማማሁት ከኢትዮ ኤሌክትሪክ ጋር ነው አለ

..* ሰበታ ከተማም አሰልጣኝ አልመረጥንም ብሏል

ከኢትዮ ኤሌክትሪክ ጋር በመስማማቴ ተደስቻለሁ የማውቀው ወደምወደው ክለብ መመለሴ ነው ሲል አዲሱ አሰልጣኝ ክፍሌ ቦልተና ተናገረ፡፡

አሰልጣኙ ከሰበታ የቀረበልኝም ጥያቄ የለም የማውቀው ኢትዮ ኤሌክትሪክ ሃላፊነቴን ስለመጀመር ነው ሲል አስረድቷል፡፡ ሰበታን አስቀድሟል የተባለውም ስህተት ነው በማለት ተናግሯል፡፡አሰልጣኙ ለማንም የተለየ ነገር አልሰጠሁም በማለትም መረጃውን አስተባብሏል፡፡

የሰበታ ከተማ ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ አለማየሁ ምንዳም ገና የተረጋገጠ ነገር የለም ክፍሌም አልተመረጠም ሁሉም ነገር የሚወሰነው ነገ ነው ለማንም የሰጠነው መረጃ የለምም ሲሉ መረጃውን አስተባብለዋል፡፡

Editor at Hatricksport

Facebook

ዮሴፍ ከፈለኝ

Editor at Hatricksport