የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ከ20 ዓመት በታች ነገ የአቋም መፈተሻ ጨዋታ ያደርጋል !

 

ከሳምንታት በፊት በአሰልጣኝ ተመስገን ዳና እየተመሩ በቀን ሁለት ጊዜ በአዲስ አበባ ስታዲየም ልምምዳቸውን እየሰሩ የሚገኙት የኢትዮጵያ ከ 20 ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድን ነገ ረፋድ የአቋም መፈተሻ ጨዋታ እንደሚያደርጉ ለማወቅ ተችሏል ።

የኢትዮጵያ ከ 20 ዓመት በታች ቡድን ካረፈበት ብሉ ስካይ ሆቴል በመነሳት ማለዳውን ወደ ደብረዘይት በማቅናት ረፋድ 3:00 ሰዓት ላይ ከ ቅዱስ ጊዮርጊስ ዋናው ቡድን ጋር የወዳጅነት ጨዋታቸውን እንደሚያደርጉ ለማወቅ ችለናል ።

Hatricksport website Editor

Twitter

kidus Yoftahe

Hatricksport website Editor