መነሻ ገጽ አፍሪካ “ተጨዋቾቼ የሚጠበቅባቸውን ጠንቅቀው የሚያውቁ ናቸው” አሰልጣኝ ፍሬው ሃ/ገብርኤል /የ20 አመት በታች ብ/ቡድን ዋና አሰልጣኝ/
አፍሪካከ 20 ዓመት በታች ሴቶችዜናዎችየኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን

“ተጨዋቾቼ የሚጠበቅባቸውን ጠንቅቀው የሚያውቁ ናቸው” አሰልጣኝ ፍሬው ሃ/ገብርኤል /የ20 አመት በታች ብ/ቡድን ዋና አሰልጣኝ/

አጋራ
አጋራ

“ሴካፋ ላይ ከነበረን ብቃት ከቦትስዋና ብሄራዊ ቡድን ጋር የነበረን አቋም የተሻለ ነው”ሲሉ አሰልጣኝ ፍሬው ሃ/ገብርኤል ተናገሩ።

የ20 አመት ሴቶች ብሄራዊ ቡድን አሰልጣኝ ፍሬው በሸራተን አዲስ በሰጡት መግለጫ “ከቦትስዋና ብሄራዊ ቡድን ጋር በነበረን የጨዋታ ሂደት ጥሩ ነበርን ሰው ሀገር ሄደን 3 ለ1 ማሸነፋችንም የሚያሳየው ይህንን ነው ከቦትስዋና ጋር ስንጫወት ለተጨዋቾቼ ስማቸውን አይተው እንዳያከብዱ ነግሬያቸዋለሁ ከእኛ በላይ እነሱ ናቸው አክብደውን የገቡት… በእስካሁኑ ውጤት ደስተኛ ነኝ ” ሲሉ ገልጸዋል።

“አሰልጣኙ ከጨመረላቸው አቅም ላይ የራሳቸውን ጨምረው የሚመጡ ተጨዋቾች አሉ እንደ ቡድን ካየነው ግን ተጨዋቾቼ የሚጠበቅባቸውን ጠንቅቀው የሚያውቁ ናቸው” ያሉት አሰልጣኙ ” የወንዶቹም ሆኑ የሴቶቹ ብሄራዊ ቡድን ላይ ለውጥ እያየንባቸው ነው የወንድ ብሄራዊ ከታላላቅ ቡድኖች ጋር ሲጫወቱ ጠንካራ ተፎካካሪ መሆናቸውን እያሳዩ ነው ቢሸነፉ እንኳን በአንድ ግብ ነው ይህም ትልቅ ለውጥ እንዳለ ያሳያል የኔ ቡድንም ለውጥ አለው ከፍተኛ እድገት እያሳየ እንደሆነ ይሰማኛል” በማለት አስረድቷል።

” በእግርኳስ በአንዴ ማደግ ብሎ ነገር የለም ቡድኑ ምን አይነት ሀሳብ አለው ? ሀሳቡንስ ተግባራዊ ያደርጋል ወይ? የሚለው ነው መታየት ያለበት ዛሬ የጠበቅነው ተጨዋች ጥሩ ላይሆን ይችላል በሂደት የሚያድግ እንጂ በአንዴ ያደገ ቡድን የለም ይሄም የእግርኳስ ባህሪ በመሆኑ ለቀጣዩ ማስተካከል ነው የሚጠበቀው” ሲል ቡድንህ አድጓል ወይ? ለተባለው ጥያቄ ምላሹን ሰጥቷል።

የ20 አመት ሴቶች ብሄራዊ ቡድን ከቦትስዋና ብሄራዊ ቡድን ጋር የሚያደርገው የመልስ ጨዋታ ከአስር ቀናት በኋላ በአዲስ አበባ ይካሄዳል ተብሎ ይጠበቃል።

አጋራ

አስተያየት ይስጡ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ተዛማጅ ጽሑፎች
ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየዲሲፕሊን ውሳኔዎችዲሲፕሊን ውሳኔ

የዲሲፕሊን ውሳኔዎች

ገዛኸኝ ደሳለኝ (ሸገር ከተማ) : ክለቡ ከ ኢትዮጵያ ቡና ጋር ባደረገው የ26ኛ...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየጨዋታ ዘገባ

የሊጉ መሪ ሲዳማ ቡና በዝናባማው ጨዋታ በመቻል ሲረታ የጣናው ሞገድም አሸንፏል

እጅግ በከባድ ዝናብ ታጅቦ በተደረገው ጨዋታ መቻል የሊጉን መሪ ሲዳማ ቡናን 3ለ1...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየጨዋታ ዘገባ

ሀድያ ሆሳዕና ፣ ፋሲል ከነማ እና ወላይታ ድቻ ወሳኝ ድል አግኝተዋል

በሊጉ የሳምንቱ የሁለተኛ ቀን መርሀግብር ሀዋሳ ከተማ ወደ ሊጉ መሪ የሚጠጋበትን ዕድል...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየጨዋታ ዘገባ

ፈረሰኞቹ በድል ሲቀጥሉ ንግድ ባንክ እና ድሬዳዋም አሸንፈዋል

ቅዱስ ጊዮርጊስ ተከታታይ ድሉን ወደ ቋቱ ሲከት ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከጨዋታ ብልጫ...