ከወራቶች በፊት የተሞሸረው ዋለልኝ ገብሬ በዝውውር መስኮቱ ጅማ አባጅፋርን የተቀላቀለ ተጨዋች ሆኗል

በኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ተሳትፎው ለኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ለኢትዮ ኤሌክትሪክ እና ለወልዋሎ አዲግራት ዩንቨርስቲ ቡድኖች ተጫውቶ ያሳለፈው ዋለልኝ ገበሬ በቤት ኪንግ ፕሪምየር ሊጉ የሁለተኛው ዙር የውድድር ቆይታ በወራጅ ቀጠናው ላይ የሚገኘውን ጅማ አባጅፋርን የተቀላቀለ ተጨዋች ሆኗል።

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ፤ ኢትዮ ኤሌክትሪክ እና ወልዋሎ አዲግራት ውስጥ በነበረው የጨዋታ ተሳትፎ ለቡድኑ ጥሩ እንቅስቃሴን ያሳይ የነበረው ይኸው ተጨዋች ከወራቶች በፊት የጋብቻ ስነ ስርዓቱን በመፈፀም ተሞሽሮ የነበረ ሲሆን አሁን ወደ ጅማ አባጅፋር ሲያመራም ለቡድኑ ጥሩ ግልጋሎቱን ይሰጣል ተብሎም ተገምቷል።

ዋለልኝ ለጅማ አባጅፋር የፈረመው ለ 1 ዓመት ጊዜ ውል እንደሆነም ተገልጿል።

Hatricksport website writer

Twitter

ዳዊት ብርሀነ

Hatricksport website writer