ቅዱስ ጊዮርጊስ እንግሊዛዊ አሰልጣኝ ሾመ

ከደቡብ አፍሪካዊ አሰልጣኝ ማሂር ዴቪድስ ጋር በስምምነት የተለያየው ቅዱስ ጊዮርጊስ አሰልጣኝ ፍራንክ ናቶል ዋና አሰልጣኝ አድርጎ ሾሟል፡፡

አሰልጣኝ ፍራንክ በእግር ኳሱ ዘርፍ ከ35 ዓመታት በላይ በተለይ በአፍሪካ በማሰልጠን በቂ ልምድ ያካበቱ ሲሆኑ፣ በርካታ ድሎችንም አሳክተዋል፡፡

እ.ኤ.አ በ 2015 እና 2016 የኬንያ ፕሪምየር ሊግ ዋንጫ ያነሱ ከመሆናቸው በተጨማሪ በ 2015 የኬንያ ሱፐር ካፕ ምርጥ ስምንት አሸናፊም ሆነዋል፡፡

እንዲሁም የእንግሊዝ ከ17አመት በታች ረዳት አሰልጣኝ በመሆን የ20111 አውሮፓ ሻምፒዮን ሆነዋል።

የ ዩ.ኤፋ ፕሮፌሽናል ላይሰንስ ያላቸው አሰልጣኝ ፍራንክ፣ ካሳኳቸው ድሎች በተጨማሪ ዌስትብሮም ፣ ሬንጀርስ እና ሚድልስቦሮው ጨምሮ ዛማሌክ ፣ ኸርትስ ኦፍ ሆክና ጎሮ ማሂያ ክለቦች በፊትነስ ፣ በ ዋና እና ምክትል አሰልጣኝነት አገልግለዋል ።

ከዚህ በተጨማሪ አሰልጣኙ በ2011 የፊፋ ኮቺንግ ኢንስትራክተር በመሆን ያገለገሉ ሲሆን በተጨማሪም የዪ.ኤፋ ኢንስትራክተር በመሆን ሰርተዋል፡፡

አሰልጣኝ ፍራንክ በዛሬው እለት ፊርማቸውን ባኖሩበት ወቅት ቅዱስ ጊዮርጊስ ስፖርት ክለብ አንጋፋ መሆኑን በመግለፅ ክለቡ የሚፈልገውን ውጤት ለማምጣትም በርትተው እንደሚሰሩ የክለቡ የፌስቡክ ገፅ አስነብቧል ።

Hatricksport website Editor

Twitter

kidus Yoftahe

Hatricksport website Editor