የሊጉ ክስተት ነገሌ አርሲ የሦስት ነባር ተጫዋቾችን ውል አድሷል።
በአሰልጣኝ ቱሉ ደስታ የሚመሩት እና ባደጉበት የመጀመሪያ አመት በኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ሁለተኛ ደረጃን በመያዝ ያጠናቀቁት ነገሌ አርሲዎች በዛሬው ዕለት አዳዲስ ተጫዋቾችን ከማስፈረማቸው በፊት የሦስት ነባር ተጫዋቾችን ውል አድሰዋል።

ግዙፉ የቀድሞው የሶዶ ከተማ እና ነቀምት ከተማ የመሐል ተከላካይ ሮሆቦት ሰላሎ ፣ የቀድሞው የጅማ አባቡና ፣ ሲዳማ ቡና ፣ ቅዱስ ጊዮርጊስ እና ኢትዮጵያ መድን አማካይ ዳዊት ተፈራ እና ሌላኛው የቀድሞው የሀምበሪቾ ዱራሜ አማካይ አለኝታ ማርቆስ ውላቸውን ያራዘሙ ተጫዋቾች ሆነዋል።
አስተያየት ይስጡ