ፋሲል ከነማ የአሰልጣኙን ውል አራዘመ።
ሦስት አሰልጣኝ ለመቅጥር ከሦስቱም ጋር መስማማት ያልቻለው ፋሲል ከነማ በመጨረሻም አሰልጣኝ ዘማርያም ወልደጊዮርጊስ ለቀጣዮቹ ሁለት አመታት ክለቡን ለማሰልጠን በዛሬው ዕለት ፊርማቸውን አኑረዋል።

ፋሲልን ከከፍተኛ ሊጉ ወደ ፕሪምየር ሊጉ ከማሳደግ ባለፈ በፕሪምየር ሊጉ ያሰለጠኑት የቀድሞው የአዳማ ከተማ ፣ ጅማ አባጅፋር ፣ ድሬዳዋ ከተማ እና ሻሸመኔ ከተማ አሰልጣኝ በአጋማሹ ከአሰልጣኝ ዮሐንስ ሳህሌ መልቀቅ በኋላ ወደ ቀድሞው ክለባቸው በመመለስ ያለፉትን ስድስት ወራት መቆየታቸው ይታወሳል።
አስተያየት ይስጡ