ግዙፉ የተከላካይ አማካይ ጋቶች ፓኖም ከፋሲል ከነማ ጋር በመለያየት ወደ ኢትዮጵያ መድኅን አምርቷል።
የወቅቱ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን አምበል ጋቶች ፓኖም በፋሲል ከነማ የአንድ አመት ቆይታ ካደረገ በኋላ በአሰልጣኝ ገብረመድህን ሀይሌ የሚሰለጥነውን ኢትዮጵያ መድኅንን መቀላቀሉ ተረጋግጧል።
ጋቶች ፓኖም በኢትዮጵያ መድኅን ለአንድ አመት የሚያቆየውን ውል መፈረሙንም ከተጫዋቹ ህጋዊ ወኪል AT Soccer Agency ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
- ማሰታውቂያ -
ተጫዋቹ በ2016 የውድድር ዘመን በአፄዎቹ መለያ በ26 ጨዋታዎች ላይ ተሰልፎ 2088 ደቂቃዎችን መጫወት ችሏል።
ጋቶች ፓኖም ከዚህ ቀደም በሊጉ ለኢትዮጵያ ቡና ፣ መቀሌ 70 እንደርታ ፣ ወላይታ ድቻ እና ቅዱስ ጊዮርጊስም ተጫውቶ ማሳለፉ የሚታወስ ነው።
የ2014 እና የ2015 የውድድር ዘመናትን ባሳለፈበት ቅዱስ ጊዮርጊስ በተከታታይ የሊጉን ዋንጫ ማሳካቱም አይዘነጋም።