መነሻ ገጽ The BiG Interview “በኢትዮጵያ ቡና መሸነፍ ቅር ቢያሰኝም በሽንፈቱ ተስፋ አልቆርጥም”አቤል ያለው
The BiG Interviewቅዱስ ጊዮርጊስቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግዜናዎች

“በኢትዮጵያ ቡና መሸነፍ ቅር ቢያሰኝም በሽንፈቱ ተስፋ አልቆርጥም”አቤል ያለው

አጋራ
አጋራ

በዮሴፍ ከፈለኝ

በጉጉት የተጠበቀው የሸገር ደርቢ በኢትዮጵያ ቡና አሸናፊነት መጠናቀቁ ቅዱስ ጊዮርጊሶችን አበሳጭቷል። ተጠባቂው ደርቢ በዝግ መካሄዱ፣ በዲ ኤስ ቲቪ መተላለፉና ጨዋታው ጠዋት መካሄዱ የደርቢው ገጠመኝ ሆኗል።በጨዋታውና እንቅስቃሴ ጥሩ አቋሙን ያሳየው አቤል ያለው በጉዳት መውጣቱና ቡድኑ መጎዳቱ ቅሬታ እንደፈጠረበት ለሀትሪክ ገልጿል። ተጨዋቹ ከሃትሪኩ ዮሴፍ ከፈለኝ ጋር በነበረው ቆይታ ስለጉዳቱና ሽንፈቱ፣ ሰለጨዋታው ዳኝነት፣ ስለ ዲ ኤስ ቲ ቪና ለተጨዋቾች የፈጠረው እድል፣ በዝግ ስለመካሄዱና ስለዋንጫው፣
ስለ ኮቪድ 19ና አባይ ግድብ፣ ስለ አዲሱ አሰልጣኝ፣ ስለተፎካካሪ ክለቦች፣ስለ ህልሙና ምኞቱ፣ስለ ኮከብ ግብ አስቆጣሪዎችና ሌሎች ጉዳዮች ምላሹን ሰጥቷል።

ሀትሪክ፦ በደርቢው ጨዋታ የደረሰብህ ጉዳት ከባድ ነው?
አቤል፦ አሁን ደህና ነኝ ከኋላዬ ታፋዬ በመገጨቱ ነው የተጎዳሁትና ልጫወት ባለመቻሌ የተቀየርኩት አሁን ደህና ነኝ።

ሀትሪክ፦ ኢትዮጲያ ቡናን እንዴት አገኘኸው?በወዳጅነት ጨዋታ በሰፊ ግብ የተሸነፈውን ይመስላል?

አቤል፦ የተለየ ሆነው ነው የመጡት ሽንፈቱ ግን ያበሳጫል ቅርም ብሎኛል ብዙ ታግለናል አልተሳካም በኢትዮጲያ ቡና መሸነፍ ቢያበሳጭም ተስፋ አንቆርጥም በቀጣይ ጠንክረን ሰርተን ጥሩ አቋም እንደሚኖረን ርግጠኛ ነኝ።

ሀትሪክ፦ዳኝነቱን እንዴት አየኸው?

አቤል፦ በጣም የተጫነን ይመስለኛል። ቀይ ካርዱም ተጋኗል ባይ ነኝ

ሀትሪክ፦ ሁለተኛው አጋማሽ ላይ ደከማችሁ እንደ መጀመሪያው አጋማሽ ጠንካራ አልነበራችሁምኮ?

አቤል፦ ጎዶሎ ሆንን ይህን ለመሸፈን ከሚጠበቅብን በላይ ጉልበታችንን አወጣን የመጀመሪያ 45 እኮ ጥሩ ነበርን 2ኛው 45 ግን ደከመን ያም ሆኖ ቀይ የወጣብን አይመስልም ነበር

ሀትሪክ፦ በጨዋታው ሂደት ከአቡኪ ጋር ትከራከሩ ነበር ሰላማዊ ነው?

አቤል፦ በደንብ አይተኸናል ማለት ነው አቡኪ ከነ አይደር ጋር ሲጨቃጨቅ ነው ተው ያልኩት እንጂ ሌላ ችግር አልነበረም።

ሀትሪክ፡-በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የገረመህ ምንድነው?

አቤል፡-በዲ.ኤስ.ቲቪ በቀጥታ መታየቱ ትልቅ እድል ነው የሰጠን.. በተቃራኒው በባዶ ስታዲየም መጫወታችን ይደብራል በሁለቱ ስሜት ውስጥ ነኝ ለኛ ለተጨዋቾች ግን በጎ ተፅዕኖ አለው፡፡

ሀትሪክ፡- ደጋፊዎቻችሁ በሌሉበት መጫወት ምን ይፈጥራል?

አቤል፡-በጣም ይደብራል ይህን አይተናል ነገር ግን ለደጋፊዎቹ የምለው ስታዲየም ሲገቡም ከጎናችን ነበሩ አሁንም ከጎናችን ናቸው ዘንድሮ ባለፉት አመታት የታጣውን ዋንጫ አግኝተን ለመካስ የተቻለንን ነገር እንደምናደርግ ልናገር እፈልጋለሁ፡፡

ሀትሪክ፡-ተጋጣሚ ተጋጣሚ ነው ከተጋጣሚ ጋር ጥሩ ግንኙነት  ሊኖር አይገባም የሚልየደጋፊ ስሜት አለ እናንተ ጋርስ?

አቤል፡- ከሜዳ ውጪና በሜዳ ላይ ስንገናኝ ስሜቱ ይለያያል ሜዳ ላይ ወንድምም ቢሆን ተፋላሚ ነው ጥግ ድረስ እንፋለማለን፡፡ ተቃራኒነቱ እስካለ ድረስ ሠላማዊ ጦርነት ይሆናል በዚህ ከደጋፊ ጋር እስማማለሁ ከሜዳ ውጪ ግን ሌላ የተለየ ህይወት ነው ባላንጣ አይደለንም፡፡

ሀትሪክ፡- በባህሪህ ዝምተኛ ወይም ጭምት የምትባል አይነት ሰው ነህ ሜዳ ላይ ግን የተለየውን አቤል ነው የማየው የጨዋታው ስሜት ይለውጥሃል እንዴ?

አቤል፡-/ሳቅ/ ሜዳ ላይ ስገባ ምንም ቢሆን ኳስ በተፈጥሮ ስሜታዊ ያደርግሃል በጣም እልህ ውስጥ ትገባለህ ሜዳና ከሜዳ ውጪ መለያየቴ እውነት ነው፡፡

ሀትሪክ፡-ሙጅብ፣ አቡበከር፣ ጌታነህ፣ አቤል… የቱ ይመስልሃል ኮከብ ግብ አግቢ የሚሆነው?

አቤል፡-/ሳቅ በሳቅ/ ገና ነው ጊዜው አሁን መናገርም ይከብዳል፡፡

ሀትሪክ፡- ምነው መሸሽ አበዛህ… ከአያያዙ የምትገምተው ሰው የለም?

አቤል፡-/ሳቅ በሳቅ/ ገናኮ ነው ለጊዜው አሁንመናገርይከብዳል፡፡

ሀትሪክ፡-በኮቪድ 19 ጊዜ ያልወፈረው አቤል ብቻ ነው የሚል ነገር ሰማሁ.. ቅጥነትህ በስፖርት የመጣ ወይስ?

አቤል፡-/ሳቅ/ እንደተጋነነው ብዙ የወፈረ የለም አባባሉ ትንሽ ተጋኗል ይህን አባባል አልቀበልም ግን ደግሞ እኔን ካየህ ትንሽ ጨምሬ ነበር በልምምድ ነው ያስተካከልኩት፡፡

ሀትሪክ፡- 7 ወር ከኳስ መገለልን እንዴት አለፍከው?

አቤል፡- ከቡድናችን ተከላካይ ሄኖክ አዱኛ ጋር ስሰራ ነበር ከርሱ ጋር ጂምም ስለምሰራ ብዙም የተጋነነ ነገር አልመጣም፡፡ በስፖርት ነው ያሳለፍኩት

ሀትሪክ፡- ቤት መዋል ለበርካቶች ችግር ቢሆንም ለአቤል ተመችቶታል የሚል ነገር ሰማሁ… እውነት ነው አልተቸገርክም?

አቤል፡-/ሳቅ/ ብዙም ጊዜ ከቤት አለመውጣቴ ጠቅሞኛል ብዙም አልተቸገርኩም የህመሙ ዜና ወሬው ይደብር ነበር በርግጥም የፈለኩትን ወጥቼ ማድረግ እንዳልችል አድርጎኛል፡፡

ሀትሪክ፡- ከቤተሰብ ጋር ወይስ ከፍቅረኛህ ጋር?

አቤል፡-ከፋሚሊ ከፋሚሊ ጋር /ሳቅ/

ሀትሪክ፡-የምን ሽሽት ነው ወደ ፍቅረኛ እንዳይኬድብህ ፈራህ?

አቤል፡-/ሳቅ/ መች ይቀራል አሁን ግን ከቤተሰቤ ጋር ነው ያሳለፍኩት፡፡

ሀትሪክ፡-በተጨዋችነት ጊዜ የበአል ቀን ጨዋታ ወይም ጉዞ ስለሚኖር ብዙም አታከብሩም ይባላል፤ ኮቪድ 19 ግን በዚህ በኩል ጠቅሟል?

አቤል፡- አዎ በፊት በአል ሲሆን ከቤተሰብ ጋር የማልገናኝበት ጊዜ ይበልጣል.. አሁን ግን በደንብ የበአል ቀን ላይ ተገኝተናል.. ገና ደግሞ ከቤተሰቤ ጋር የልደት በዓልን አከብራለሁ፡፡
ሀትሪክ፡-የዲ.ኤስ.ቲቪ መምጣት ለአቤል አሪፍ እድል ነው?
አቤል፡- ምን ለኔ ብቻ? ለሁሉም ተጨዋች ከሰራን ጥሩ እድል ይመስለኛል…

ሀትሪክ፡-አይ ላንተ ያልኩት እድሜያቸው የገፉትን ተጨዋቾች አይመለከትም ብዬኮ ነው?

አቤል፡-/ሳቅ በሳቅ/እውነት ነው… ለኔም ለተጨዋቾችም ከሀገር ውጪ ወጥቶ የመጫወት እድልን ይፈጥራል

ሀትሪክ፡- እስካሁን የውጪው እድል አልተገኘም?

አቤል፡-ኧረ ተገኝቷል ግን ጊዜው ገና ነው በሚል ትቼዋለው፡፡

ሀትሪክ፡-ከጊዮርጊስ ጋር ምን ታልማለህ?
አቤል፡-በክለቡ ላይ ታሪክ እንደሰሩት እንደበፊቶቹ ትልልቅ ተጨዋቾች ታሪክ መስራት እፈልጋለው ገና የምሰራቸው ታሪኮች ከፊቴ አሉ፡፡

ሀትሪክ፡- ከፈረሰኞቹ ጋር ማሳካት እፈልጋለሁ የምትለው 3 ነገሮችን ግለፅ?

አቤል፡- ዋናው ፕሪሚየር ሊግን ነው ሁለተኛ በቀጣዩ አመት በሚካሄደው ሻምፒዮንስ ሊግ መሳተፍ ነው 3ኛው በዚሁ ውድድር ላይ ካሁን በፊት ከሄድንበት ደረጃ በተሻለ መልኩ መግፋት እፈልጋለሁ፡፡

ሀትሪክ፡-ጉዳት የሚያሰጋህ አይነት ተጨዋችነህ?

አቤል፡- አይደለሁም… ብዙም አጋጥሞኝ አያውቅም ሁሉንም ጨዋታዎች ላይ ተሳትፌ ቡድኔን አገልግያለሁ፡፡

ሀትሪክ፡- አቤል 2013 የኔ አመት ነው ብለህ ታምናለህ?

አቤል፡-/ሳቅ በሳቅ/ የኔ ሳይሆን የቅዱስ ጊዮርጊስ ነው /ሳቅ/ቅድሚያ የምሰጠው ለቅዱስ ጊዮርጊስ ድል ነው ከዚያ በኋላ ድሉን ስናረጋግጥ ወደግል እንሄዳለን?

ሀትሪክ፡- ተጨዋቾቹበሙሉልብየሚያስቡትይሄንነው?

አቤል፡-ሁሉም የቅዱስ ጊዮርጊስ ተጨዋቾች ከግላቸው ክብር ይልቅ ለቡድኑ ድል የሚያስቀድሙ ናቸው በዚህ ርግጠኛ ነኝ፡፡ 3 አመት ያለ ዋንጫ መቆየታችን የፈጠረብን የቁጭት ስሜት አለ የሊጉን ዋንጫ ካነሳን ለኔ የመጀመሪያ ጊዜ በመሆኑ ጓጉቻለሁ የልፋታችን መጨረሻ ዋንጫ በመሆኑ ፍላጎቴን ለማሳካት እጥራለሁ ቡድኑ የዋንጫ ችግር ባይኖርበትም ዋንጫ ያላገኙ ተጨዋቾች በመኖራቸው ዋንጫውን ለመረከብ ተዘጋጅተናል ከፈጣሪ ጋር ይሳካል ብዬ አስባለው፡፡

ሀትሪክ፡-ለ4ኛ አመት ዋንጫ የማጣት ስጋት የለብህም?

አቤል፡-/ሳቅ/ በፍፁም የለም እንደቡድን ስለምንጫወት የምንሰጋበት ነገር የለም፤ የምንቸገር አይመስለኝም፡፡

ሀትሪክ፡-የዋንጫ ማጣት ሀትሪክ አይሰራብኝም እያልክ ነው?

አቤል፡-/ሳቅ/ አዎ አይሰራብኝም በፍፁም…. ዋንጫውን ለመውሰድ ዝግጁ ሆነን ነው ወደ ውድድር የገባነው፡፡

ሀትሪክ፡-አሁን ድረስ ከቅዱስ ጊዮርጊስ የሚገርምህ ምንድነው?

አቤል፡- ከሀገራችን ክለቦች ጊዮርጊስን የሚመስል አላየሁም ትልቅና ፕሮፌሽናል የሆነ ክለብ ነው ያስቀመጠውን ግብ ለማሳካት ይጥራል አመራሮቹ ለተጨዋቾቹ ያላቸው ክብርና ክትትል የተለየ ያደርገዋል፡፡ እንኳን ሽንፈት አቻ መውጣት የማይቻልበት ክለብ ነው ይሄ ይገርመኛል፡፡

ሀትሪክ፡- አዲሱ አሰልጣኝ ላንተ ተመችቶሃል?

አቤል፡- አዎ ሁሉም አሰልጣኞች የየራሣቸውን ነገር ይዘው ይመጣሉ፤ በፈለጉት መንገድ ሊያጫወቱም ይችላሉ የአሁኑ አሰልጣኝ ጎበዝ ነው ወጣትም እንደመሆኑ ሁሉንም ነገር ይረዳል የተሻለ ነገር እያስተማረን ይገኛል እኔ ብቻ ሳልሆን ጓደኞቼም ጥሩ ትምህርት እያገኙ ነው በዚህም ጥሩ እውቀት አግኝተናል ማለት ይቻላል፡፡

ሀትሪክ፡- በተጨዋችነት ደረጃ ላይ በኔ ላይ ተፅዕኖ ፈጥረዋል ብለህ የምታደንቃቸው አሰልጣኞች አሉ?

አቤል፡- አሰልጣኝ ዮሀንስ ሳህሌ፣ /ነፍሱን ይማረውና/ አሰልጣኝ ንጉሴ ደስታ፣ አብርሃም መሀመድ ኪንግ እንዲሁም በታዳጊነት አቃቂ ማዞሪያ ያሰለጠነኝን አለማየሁ /ሚሌ / ትልቅ አስተዋፅኦ አድርገውልኛል፡፡

ሀትሪክ፡- እንደ ተጨዋች ከማን ጋር መጣመር ደስ ይልሃል?

አቤል፡-ከነ ጌታነህ ከበደ፣ አማኑኤል ገ/ሚካኤልና አዲስ ግደይ ጋር ጥሩ ግንኙነትና ጥምረት አለኝ ከእነርሱ ጋር ባለኝ ጥምረት ደስ ይለኛል፡፡

ሀትሪክ፡-ጥያቄውን እየሸሽህ ነው..?

አቤል፡- ከጌታነህ ውጪ ከነ አዲስና አማን ጋር በብሔራዊ ቡድን ደረጃ ተጫውቻለሁ አቃቸዋለሁ ለዚህ ነው የጠራሁልህ /ሳቅ/

ሀትሪክ፡-በቅዱስ ጊዮርጊስ ላሳካው እፈልጋለሁ የምትለው ክብር የሳላህዲን ሰይድ ወይስ የአዳነ ግርማ?

አቤል፡- ስም የምጠቅሰው የለም የራሴን ታሪክ ለመስራት የምችለውን አደርጋለሁ እንትና ማለትን ግን አልሻም፡፡

ሀትሪክ፡- በአንድ ክለብ ውስጥ የማይነካ ታሪክ የከሰተ ተጨዋች ቢኖር ሁሉም ይህን ሪከርድ መብለጥ ይፈልጋል አንተጋስ በዚህ ደረጃ የእገሌ የምትለው የለም?

አቤል፡-የለም.. ምንም… የራሴን ታሪክ የመከሰት እንጂ የእነ እንተናን የምለውየምጠቅሰው ነገርየለም

ሀትሪክ፡-የቅዱስ ጊዮርጊስ የዋንጫ ድል ስንት ጨዋታ እየቀረው ይረጋገጣል?

አቤል፡-/ሳቅ/ ይሄ ኳስ ነው አይገመትም ማሸነፋችን አይቀርም ስንት ጨዋታ እየቀረው የሚለውን መገመት ግን ከባድ ነው፡፡

ሀትሪክ፡- ከፋሲል ሽንፈት በኋላ ነቃችሁ ልበል 4-4-3 ግብ አስቆጠራችሁ አሰላለፍ መሰለኮ?

አቤል፡- /ሳቅ በሳቅ/ በጣም አንቅቶናል 3 አመት አካባቢ የመጀመሪያጨዋታንማሸነፍባለመቻላችንይህንታሪክለማስተካከልጓጉተንስለነበርስሜታዊሆነንገብተንተሸነፍንከዚያበኋላእንደሁሌውምቁጭብለን ተነጋግረን የተሻለ ውጤት ለማምጣት ችለናል ከዚህም በኋላ በተሻለ መልኩ የሚቀጥል ይሆናል ብለን እናስባለን፡፡ በርካታ ግብ እያስቆጠርን ማሸነፍም ችለናል የምንችለው እናደርጋለን ስብስቡ ከበርካታ አቅጣጫ ግብ ማስቆጠር የሚችል መሆኑ ደግሞ የተሻለ እንድንጥር አድርጎናል ከአቅም በላይ በሆኑ ጥረት ውጤታማ እየሆን ነው እኔ ብወጣ የሚገባው ተጨዋች ከኔ የተሻለ አንጂ የሚያንስ አለመሆኑ በድል እንድንጓዝ አድርጎናል ለመሰለፍ የሚደረግ ፉክክርም መኖሩ ውጤታማ አድርጎናል፡፡

ሀትሪክ፡- ቅዱስ ጊዮርጊስ ዋንጫ እንዳይወስድ የሚያደርግ ስጋት የሚፈጥር ክለብ አለ?

አቤል፡- አይ በርሱ በኩል ስጋት የለብንም በርግጥ ማንንም አንንቅም ጥሩ ሆነን ሁሉን እኩል አይተን ስለምንገባ ማሸነፋችን የግድ ይሆናል ሁሉም ተጋጣሚያችን ተፋላሚያችን በመሆኑ ከሁሉም 3 ነጥብ መውሰድ የግድ ይላል በዚህ ምክንያት ለይተን የምንጠራው የለም ሁሉን ረተን ዋንጫ ለማንሣት ግን ተዘጋጅተናል፡፡

ሀትሪክ፡- አብሬያቸው ብጫወት የምትላቸው ተጨዋቾች አሉ?

አቤል፡- ብዙዎቹን በክለብም ይሁን በብሔራዊ  ቡድን ደረጃ ስላገኘኋቸው አብሬው ብጫወት የምለው የለም፡፡

ሀትሪክ፡- እያየህ ያደከው ተምሣሌት የሆነህ ተጨዋች አለ?

አቤል፡-ክርስትያኖ ሮናልዶ ነዋ ልጅ ሆኜ የውጪ ኳስ ነው የማየውና የምወደው በዚህም የክርስቲያኖ ሮናልዶ ታታሪነትና ጥረት እንደምሳሌ ሆኖኛል ማለት እችላለሁ፡፡በሀገር ውስጥ ግን ተምሳሌት የለኝም በሀገር ውስጥ የማየው ጨዋታም አልነበረም

ሀትሪክ፡- እንደ ሮናልዶ ታታሪ ነህ?

አቤል፡- እሱ ምርጥ የተጨዋች ተምሣሌት ነው ታታሪና ስራውን አክባሪም ነው እኔም እንደርሱ የሆንኩ ይመስለኛል /ሳቅ/

ሀትሪክ፡-በጨዋታ ወቅት ያለው ፍጥነትህ የልምምድህ ውጤት ነው ማለት ይቻላል?

አቤል፡- ኧረ አይደለም ልምምድ ላይ ብዙም አይደለሁም ያን ያህልም አልሮጥም በግጥሚያ ወቅት ግን ጥሩ ነኝ /ሳቅ/

ሀትሪክ፡-ክፉ አመሎች በተለይ ለኳስ ተጨዋች የማይጠቅሙ እንዲሁም ለዕድሜያቸው ማጠር የሚዳርገው በቂ እረፍት አለማግኘት አንተን አይመለከትህም.. ለዚህ ይሆን የጠቀመህ?

አቤል፡-/አዎ/ አዎ በማረፍ የሚገኘው ጥቅምን ሁሉም ተጨዋች ያውቀዋል ብዙ ጊዜ ተኝቼ እረፍት እወስዳለሁ እውነትም ጠቅሞኛል፡፡

ሀትሪክ፡- የመንፈሳዊ ህይወትህም ለዚህ ጠቅሞሀል ማለት ይቻላል?

አቤል፡- ምንም ጥያቄ የለውም በደንብ ጠቅሞኛል ጠንካራ የምባል ባልሆንም መንፈሳዊ ህይወቴ ጥሩ ነው እግዚአብሔር እፈራለሁ ይሄ በደንብ ጠቅሞኛል፡፡

ሀትሪክ፡-አቶ አብነት ገ/መስቀል የአርሰናል ደጋፊ ናቸው አንተስ የማን ደጋፊ ነህ?

አቤል፡-የማን.ዩናይትድ /ሳቅ/

ሀትሪክ፡-ሁለታችሁ በገጠመኝ ስለ ክለቦቹ አውርታችሁታውቃላችሁ?

አቤል፡-/ሳቅ/ አንድም ቀን አውርተን አናውቅም ስለ ውጪ ኳስም አናውራም

ሀትሪክ፡-በማን.ዩናይትድ በምኑ ተማረክ?

አቤል፡- ትዝ አይለኝም ምክንያቱንም አላውቅም ከልጅነቴ ጀምሮ ግን ደጋፊያቸው ነኝ፡፡

ሀትሪክ፡-ውጤታማና ተፈሪ መሆናቸው የቀነሰ አይመስልህም?

አቤል፡-አዎ…ከሰር አሌክስ ፈርጉሰን በኋላ ጥሩ አይደሉም አሁን ግን ወደ ጥሩ አቋም እየተመለሱ በመሆኑ ደስተኛ ነኝ፡፡

ሀትሪክ፡-የዳኝነቱን ጉዳይ እንዴት አየኸው?

አቤል፡-/ሳቅ/ ሁሉም በዲ.ኤስቲቪ እየተጋለጠ ነው በርግጥ ስህተት ሁሌም አይጠፋም ተጫዋቹ ከስህተቱ እንደሚታረመው ዳኞቹም ከስህተታቸው እንደሚታረሙ ተስፋ አደርጋለሁ፤ ስህተቱ ግን ተጋንኖ መስፋት አለበት ብዬ አላምንም የሁሉም ስህተት በዲ.ኤስ.ቲቪ እየታየ ነው በተቻለ መጠን ተሻሽሎ ለመገኘት የሁሉም ጥረት ይጠበቃል፡፡

ሀትሪክ፡-ጨረስኩ.. የመጨረሻ ቃል?

አቤል፡-ለዚህ ያደረሰኝን በጤና የጠበቀኝን ፈጣሪን ማመስገን እፈልጋለሁ፡፡ለመላው የክርስትና ሃይማኖት ተከታዮች እንኳን ለብርሃነ ልደቱ አደረሳችሁ ማለት እፈልጋለው

ስለ አባይ ግድብ 
በጣም ደስ ያለኝ ጊዜ ነው.. ብዙ ዋጋ የተከፈለበት ነገር በመሆኑ እንደ ሀገር ደስ የሚል ዜና ነው እኛም ይህን ስላየን እድለኞች ነን፤ ህብረተሰቡም በሚገባ ሊደግፈው ይገባል በኔ በኩል በ8100A በደንብተሳታፊ ነኝ ት/ቤት እያለሁም ቦንድ ገዝተናል ትልቅ የህዝብ ርብርብ ያለበት የሁሉም እጅ የተሳተፈበት እንደመሆኑ እስከፍፃሜው ሊደገፍ ይገባል ባይ ነኝ፡፡

ስለ ኮቪድ 19 
አሁን ከሰው ጥንቃቄ በላይ የቫይረሱ መስፋፋት እየጨመረ በመሆኑ መስተካከልና አካሄዳችንን መቀየር አለብን ህብረተሰቡ ማክስ በማድረግ ርቀት በመጠበቅና እጆቹን በሳኒታይዘር በማጽዳት ጥንቃቄ ማድረግ አለበት እግዚአብ ሄርም በጣም ጠብቆናል ልናመሰግነው ይገባል ፈጣሪ ከኛ ጋር ባይሆን ኖሮ እንደ አመጣጡ ወይም ሌላ ቦታ እንዳደረሰው ጉዳት ቢሆን በጣም ከባድ ይሆን ነበር ከጥንቃቄ ጋር እግዚአብሄር አሁንም ይጠብቀን ማለት እፈልጋለሁ፡፡

አጋራ

አስተያየት ይስጡ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ተዛማጅ ጽሑፎች
ሽረ ምድረገነትዜናዎችየኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ

ምድረ ገነት ሽረ ከኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ ውድድር ውጭ ሆነ!

በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ሲሳተፍ የነበረው እና በተጠናቀቀው የውድድር አመት ከኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ...

መቻልኢትዮጵያ ቡናዜናዎችየዝውውር ዜናዎች

ሁለቱን ተጫዋቾች ሁለቱ ክለቦች ተካፈሉ

ለሁለት ክለብ በመፈረማቸው ቅጣት ላይ የነበሩት ተጫዋቾች ለመቻል እና ለኢትዮጲያ ቡና እንዲጫወቱ...

ካፍዜናዎች

የኒጀር እና ሞሮኮ ጨዋታ በኢትዮዽያዊያን ዳኞች ሊመራ ነው

ራቫት ላይ የሚደረገው ወሳኙ የአፍሪካ ዋንጫ የማጣሪያ ጨዋታ በኢትዮዽያዊያን ዳኞች ይመራል። ኬኒያ...