በቂ የመጫወት ዕድሎችን በተለያዩ ምክንያቶች ማግኘት ያልቻለው ሱራፌል ዳኛቸው ከአሜሪካው ክለብ ጋር ተለያይቷል።
ከትንሿ መርቲ ከተገኘ በኋላ የእግር ኳስ ህይወቱን በአዳማ ከተማ በመምራት ከብዙሀኑ ጋር መተዋወቅ የቻለው የአማካይ ስፍራ ተጫዋቹ ሱራፌል ዳኛቸው ከፋሲል ከነማ ጋር ከተለያየ በኋላ ወደ አሜሪካን አምርቶ ኢትዮጵያዊው ጆ ማሞ ካቻ በቦርድ አባልነት በሚመሩት በአሜሪካው የታችኛው የሊግ ዕርከን ዩሲኤል ላይ ለሚሳተፈው ሎዶን ዩናይትድ ውስጥ ቢያሳልፍም ክለቡ በጋራ ስምምነት መለያየትን መርጦ ሱራፌልን ጨምሮ ከአስራ ሁለት ተጫዋቾች ጋር መለያየቱ ታውቋል።
በጉዳት እና ሌሎች ምክንያቶች በቂ ግልጋሎትን ለአሜሪካው ክለቡ መስጠት ያልቻለው አማካዩ ቀጣዩ መዳረሻው የሀገር ውስጥ ክለብ አልያም ደግሞ አዲሱ የአሰልጣኝ ውበቱ አባተው የላይቬሪያው ሊሼር ክለብ ሊሆን እንደሚችል ይጠበቃል።



