… ከሳሹ ወገን ዛሬ ቦርዱ ሃላፊነቱን መልቀቁን በይፋ ማሳወቅ አለበት እያለ ነው ….
*…. ሌላው ወገን የቦርዱ መልቀቅ በጠቅላላ ጉባኤ የሚወሰን እንጂ አሁን የሚለቅ የለም እያሉ ነው …
ቅዱስ ጊዮርጊስ ውስጥ ተፈጥሮ የነበረውን ልዩነት በሰላም የመፍታት ጉዞ ሳንካ ገጠመው።
ከታማኝ ምኔጭ በተገኘ መረጃ ቦርዱ ስልጣኑን በመልቀቅ የመፍትሄው አካል ይሆናል ሲባል እሰከዚህ ዘገባ ድረስ ዝምታን መርጧል። ቦርዱ ዛሬ ስህጣኑን መልቀቁን ሊያሳውቅ ነገ አራት ሰአት በአዲስ አበባ ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ሃላፊዎችና 8 ተወያዮች ከሁለት ሼማግሌዎች ጋር ሊወያዩ በጁፒተር ሆቴል በፌዴሬሽኑ ፕሬዝዳንት ኢሳያስ ጅራ የተያዘው ቀጠሮ መያዙ እና መጋቢት 21/2018 ባለው የፍርድ ቤት ቀጠሮ ከሳሹ ወገን ክሱን ሊያነሳ ታስቦ የነበረ ቢሆንም የመሳካቱ ነገር አጠራጣሪ ሆኗል።
ዘገባውን እስካጠናከርንበት ሰአት ድረስ ቦርዱ ዝምታን በመምረጡ የተያዘው ውይይት ላይካሄድ እንደሚችልና የተያዘው የፍርድ ቤቱ ክስ እንደሚቀጥል መረጃዎች ይገልጻሉ።
ቦርዱን በፕሬዝዳንትነት የመሩት አቶ አብነት ገ/መስቀል ከውይይቱ በኋላ ሃላፊነታቸውን ማስረከባቸው የፈጠረው ብርሃን ዳግም ችግር ገጥሞታል።
በቦርዱ ወገን ያሉ ወገኖች ግን ዛሬ የሚለቅ የቦርድ አባል እንደሌለ እስከ ጠቅላላ ጉባኤ ድረስ በስራው ላይ እንደሚቀጥልና አቶ ንዋይ በየነ በቼክ ፈራሚነታቸወ እንደሚቀጥሉ የነገው ውይይት የመፍትሄ ማፈላለግና ቀጣይ ስራ ላይ የሚደረግ ስብሰባ ነው ሲሉ ይገልጻሉ።
ሁሉም ወገኖች ታሪካዋውን ክለብ ለማዳነ በሚደረገው ጥረት ውስጥ የመፍትህው አካል እኔዲሆኑ ብዙሃኑ ደጋፊ ጠይቆ አንድ ክለብ አንድ ቤተሰብ የሚለው እሳቤ እንዲተገበር አሳስቧል።
አስተያየት ይስጡ