መነሻ ገጽ መቐለ 70 እንደርታ መቐለ ኮትዲቫራዊ አጥቂ አስፈረመ
መቐለ 70 እንደርታዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ

መቐለ ኮትዲቫራዊ አጥቂ አስፈረመ

አጋራ
አጋራ

በጊዜያዊ አሰልጣኙ ፀጋዬ ኪዳነማርያም ተስፋ የቆረጠው መቐለ 70 እንደርታ ሦስተኛ ፈራሚውን አገኘ።

በጊዜያዊ አሰልጣኙ ፀጋዬ ኪዳነማርያም ደስተኛ ያልሆነው መቐለ 70 እንደርታ የአጋማሹ ሦስተኛ ፈራሚውን የግሉ አድርጓል። የ28 አመት ዕድሜ እንዳለው የሚነገርለት የፊት እና የመስመር አጥቂው ባምባ አብዱለጢፍ ነው ክለቡን የተቀላቀለው።

ለሀገሩ ክለብ ስታድ አቢጃን ፣ አር ሲ አቢጃን ፣ አሴክ ሚሞሳ ፤ ለአንጎላው ሳጋርዴን ለደቡብ አፍሪካው ቲ ኤስ ጋላክሲ በሊቢያው አልሱልፋም እና ለጋናው አዱዋና ስታር ከተጫወተ በኋላ ወደ ሀገሩ ተመልሶ ያለፉትን ወራት ለቀድሞው ክለቡ ስታድ አቢጃን በመጫወት ላይ የነበረው ይህ አጥቂ እስከ ሰኔ ወር መጨረሻ መቐለ 70 እንደርታን መቀላቀሉ ይፋ ተደርጓል።

ከክለቡ ጋር በተያያዘ በአሰልጣኝ ፀጋዬ ኪዳነማርያም ደስተኛ መሆን ያልቻሉ የክለቡ ደጋፊዎች ከሰሞኑ ወደ ክለቡ ፅህፈት ቤት ተጉዘው በክለቡ ደካማ ውጤት ዙሪያ ከአመራሩ ጋር መወያየት የቻሉ ሲሆን ጊዜያዊ ሆነው የተሾሙት አሰልጣኝም በቀጣይ የስንብት በትር ሊያርፍባቸው ይችላልም ተብሎ ይጠበቃል።

አጋራ

አስተያየት ይስጡ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ተዛማጅ ጽሑፎች
ሽረ ምድረገነትዜናዎችየኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ

ምድረ ገነት ሽረ ከኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ ውድድር ውጭ ሆነ!

በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ሲሳተፍ የነበረው እና በተጠናቀቀው የውድድር አመት ከኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ...

መቻልኢትዮጵያ ቡናዜናዎችየዝውውር ዜናዎች

ሁለቱን ተጫዋቾች ሁለቱ ክለቦች ተካፈሉ

ለሁለት ክለብ በመፈረማቸው ቅጣት ላይ የነበሩት ተጫዋቾች ለመቻል እና ለኢትዮጲያ ቡና እንዲጫወቱ...

ካፍዜናዎች

የኒጀር እና ሞሮኮ ጨዋታ በኢትዮዽያዊያን ዳኞች ሊመራ ነው

ራቫት ላይ የሚደረገው ወሳኙ የአፍሪካ ዋንጫ የማጣሪያ ጨዋታ በኢትዮዽያዊያን ዳኞች ይመራል። ኬኒያ...