ቅዱስ ጊዮርጊስን እስከ ተጠናቀቀው የውድድር ዘመን ድረስ ያገለገለው አማካይ ለፊፋ ያቀረበው ክስ ክለቡ ላይ እግድ እንዲጣል አድርጓል።
ወደ ኢትዮጵያ መጥተው በፕሪምየር ሊጉ ማገልገል ከቻሉ የውጪ ዜጋ ተጫዋቾች መካከል ጋናዊው አማካይ ክዋሜ ፍሪምፓንግ አንዱ ነው። የሀገሩን ክለብ አዱዋና ስታርስን ለቆ ቅዱስ ጊዮርጊስን በመቀላቀል እስካለፈው የውድድር ዘመን ድረስ ሲጫወት የነበረው ተጫዋቹ በክለቡ የፈፀመው ውል በአግባቡ አለፈፀሙን ተከትሎ በአሁኑ ሰዓት ያለ ክለብ የሚገኘው አማካዩ በውሌ መሠረት ጥቅማጥቅሜ ይከበርልኝ ሲል ለፊፋ ባቀረበው ክስ መነሻነት የአለም አቀፉ የእግር ኳስ የበላይ አካል ቅዱስ ጊዮርጊስ በዝውውሩ እንዳይሳተፉ ውሳኔን አሳልፏል።
ውሳኔው የማይፈፀም ከሆነ ተጨማሪ ውሳኔዎች ሊኖሩ እንደሚችሉም ያገኘነው መረጃ አመላክቷል።


- ማሰታውቂያ -


