የዲሲፕሊን ውሳኔዎች
1.ካሌብ አማንክዋሀ (ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ): ቅዳሜ ኅዳር 27 2018 ዓ.ም. ክለቡ ከ ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርስቲ ጋር ባደረገው የ9ኛ ሳምንት እግርኳስ ጨዋታ በ 46 ኛ ደቂቃ ላይሁለተኛ ቢጫ ካርድ የሚያስጥ ጥፋት በመፈፀሙ በቀይ ካርድ ከጨዋታ ሜዳ የተወገደ ስለመሆኑ ሪፖርት ቀርቦበታል ።
ስለሆነም ተጫዋቹ ለፈፀመው ጥፋት በኢ.እ.ፌ ዲሲፕሊን መመሪያ ክፍል 2 ምዕራፍ 2 አንቀፅ 35(መ) መሰረት 1 ጨዋታ እንዲታገድ የየውድድርና ስነስርዓት ኮሚቴ ወስኗል።
2.ረመዳን የሱፍ(ኢትዮጵያ መድን ): ረቡዕ ታህሳስ 1 2018 ዓ.ም. ክለቡ ከ ሸገር ከተማ ጋር ባደረገው የ3ኛ ሳምንት እግርኳስ ጨዋታ በ 88 ኛ ደቂቃ ላይሁለተኛ ቢጫ ካርድ የሚያስጥ ጥፋት በመፈፀሙ በቀይ ካርድ ከጨዋታ ሜዳ የተወገደ ስለመሆኑ ሪፖርት ቀርቦበታል ። ስለሆነም ተጫዋቹ ለፈፀመው ጥፋት በኢ.እ.ፌ ዲሲፕሊን መመሪያ ክፍል 2 ምዕራፍ 2 አንቀፅ 35(መ) መሰረት 1 ጨዋታ እንዲታገድ የየውድድርና ስነስርዓት ኮሚቴ ወስኗል።
3.ዳዊት ማሞ (መቻል) : ከታች በተጠቀሱት 5 ጨዋታዎች የቢጫ ማስጠንቅቂያ ካርድ ተመልክቷል።
- ማሰታውቂያ -
- መቐለ 70 እንደርታ መቻል
- መቻል-ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ
- መቻል-ፋሲል ከነማ
- ምድረ ገነት ሽረ -መቻል
- ሃዋሳ ከተማ-መቻል
ስለሆነም ተጫዋቹ ለፈፀመው ጥፋት በኢ.እ.ፌ ዲሲፕሊን መመሪያ ክፍል 2 ምዕራፍ 3 አንቀፅ 35 (ሠ) መሰረት 1 ጨዋታ እንዲታገድ በተጨማሪ የገንዘብ ቅጣት ብር 1500 እንዲከፍል የውድድርና ስነስርዓት ኮሚቴ ወስኗል።
4.ፍቃዱ መኮንን (ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርስቲ): ከታች በተጠቀሱት 5 ጨዋታዎች የቢጫ ማስጠንቅቂያ ካርድተመልክቷል።
- ምድረ ገነት ሽረ-ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርስቲ
- ድሬደዋ ከተማ-ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርስቲ
- ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርስቲ-ሃዋሳ ከተማ
- ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርስቲ-መቐለ 70 እንደርታ
- ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ‐ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርስቲ
ስለሆነም ተጫዋቹ ለፈፀመው ጥፋት በኢ.እ.ፌ ዲሲፕሊን መመሪያ ክፍል 2 ምዕራፍ 3 አንቀፅ 35(ሠ) መሰረት 1 ጨዋታ እንዲታገድ በተጨማሪ የገንዘብ ቅጣት ብር 1500 እንዲከፍል የውድድርና ስነስርዓት ኮሚቴ ወስኗል።
5.ሰመረ ሀፍተይ (ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርስቲ) : ከታች በተጠቀሱት 5 ጨዋታዎች የቢጫ ማስጠንቅቂያ ካርድተመልክቷል።
- ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርስቲ-ሲዳማ ቡና
- ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርስቲ-መቻል
- ድሬደዋ ከተማ-ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርስቲ
- ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርስቲ-መቐለ 70 እንደርታ
- ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ‐ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርስቲ
ስለሆነም ተጫዋቹ ለፈፀመው ጥፋት በኢ.እ.ፌ ዲሲፕሊን መመሪያ ክፍል 2 ምዕራፍ 3 አንቀፅ 35(ሠ) መሰረት 1 ጨዋታ እንዲታገድ በተጨማሪ የገንዘብ ቅጣት ብር 15ዐዐ እንዲከፍል የውድድርና ስነስርዓት ኮሚቴ ወስኗል።
6. ኢትዮጵያ መድን ክለቡ ከሸገር ከተማ ጋር ባደረገው የ3 ኛ ሳምንት እግርኳስ ጨዋታ የኢትዮጵያ መድን ቡድን ተጫዋች የሆኑት
- አማኑኤል ኤርቦ
- በረከት ካሌብ
- ረመዳን የሱፍ
- ረመዳን የሱፍ
- ፋሲል ገብረሚካኤልበተለያዩ ጥፋቶች ካርድ የተሰጣቸው በመሆኑ በኢ.እ.ፌ ዲሲፕሊን መመሪያ ክፍል 3 ምዕራፍ 3 አንቀፅ 65 (ሀ) መሰረት የገንዘብ ቅጣት ብር 5000 / አምስት ሺ/እንዲከፍል የውድድርና ስነስርዓት ኮሚቴ ወስኗል፡፡
7 . ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ክለቡ ከወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርስቲ ጋር ባደረገው የ9 ኛ ሳምንት እግርኳስ ጨዋታ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቡድን ተጫዋች የሆኑት
- ሲሞን ፒተር
- ካሌብ አማንክዋህ
- ካሌብ አማንክዋህ
- ፓላክ ቾል
- ናትናኤል ዳንኤል
- ቢኒያም ካሣሁን
በተለያዩ ጥፋቶች ካርድ የተሰጣቸው በመሆኑ በኢ.እ.ፌ ዲሲፕሊን መመሪያ ክፍል 3 ምዕራፍ 3 አንቀፅ 65 (ሀ) መሰረት የገንዘብ ቅጣት ብር 5000/ አምስት ሺ/ እንዲከፍል የውድድርና ስነስርዓት ኮሚቴ ወስኗል፡፡
8.ፋሲል ከነማ: ክለቡ በ9ኛ ሳምንት መርሀ ግብር ቅድመ ጨዋታ ስብሰባ ላይ ስላለመገኘቱ ሪፖርት ቀርቦበታል።
ስለሆነም ከለቡ ለፈጸመው ጥፋት በፕሪምየር ሊግ የውድድር ደንብ ክፍል 1 አንቀፅ 10 ተቁ 7 መሰረት ብር 5000/አምስት ሺህ/ እንዲከፍል የውድድርና ስነስርዓት ኮሚቴ ወስኗል።


