ለመጀመሪያ ጊዜ በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ተሳትፎ በማድረግ ላይ የሚገኘው ሸገር ከተማ በ17 ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድን ድንቅ ብቃታቸውን ያሳዩ 3 ተጫዋቾችን በይፋ አስፈርሟል።
በአፍሪካ ዋንጫ የሴካፋ ዞን የማጣሪያ ውድድሩ ኮከብ ተጫዋች ሆኖ የተመረጠው ቢንያም አብርሀ ፤ ጥምር ኮከብ ግብ አስቆጣሪው ዳዊት ካሳው እና ዘላለም መንግስቱ ሸገርን የተቀላቀሉ ተጫዋቾች ናቸው።
ሸገር ከተማ ዳዊት ካሳው እና ቢንያም አብርሀን ለዚህ ደረጃ ላበቃው ስሪ ፖይንት አካዳሚ ተጫዋቾቹን የግሉ ለማድረግ በድምሩ አንድ ሚልዮን ብር ከፍሏል።
በተጨማሪም ሶስቱም ተጫዋቾች ወርሐዊ የ50 ሺህ ብር ደመወዝ ተከፋይ ሆነው ለሶስት ዓመት በክለቡ የሚያቆያቸውን ውል ፈርመዋል።
- ማሰታውቂያ -






