“የሲዳማ ቡና ቆይታዬ አሁን ላይ እርግጠኛ ሆኜ መናገር ባልችልም ልቤ ግን ሲዳማ ቡና ነው ያለው።”ዩሴፍ ዮሐንስ /ሲዳማ ቡና

“የሲዳማ ቡና ቆይታዬ አሁን ላይ እርግጠኛ ሆኜ መናገር ባልችልም ልቤ ግን ሲዳማ ቡና ነው ያለው።”

 “የሙልጌታ ምህረትን አይነት የጨዋታ ዘይቤ ይዤ ነው መጫወት እምፈልገው”

“ለኔ ትልቁ አሰልጣኜ ዘርአይ ሙሉ ነው”
ዩሴፍ ዮሐንስ /ሲዳማ ቡና


እንግዳችን ለመሆን ፍቃድኛ ስለሆንክ በሀትሪክ ስፖርት ስም ከልብ አመሰግናለው።በቅድሚያ ስለ ትውልድ እና እድገትህ እንዲሁም የእግር ኳስ ጅማሬክ ምን ይመስላል?

“እኔም እንግዳችሁ ስላደረጋችሁኝ አመሠግናለሁ። ትውልዴ በሸበዲኖ ወረዳ ሲሆን እድገቴ በሀዋሳ ዙሪያ ልዩ ስሙ ዶሬ ባፋና ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ነው።የእግር ኳስ ጅማሬ እንደ ማንኛውም ታዳጊ ከትምህርት ቤት ጀምሮ ነው ከዛም በፕሮጀክት ደረጃ ሀዋሳ ተስፋ ቡድን ነበር ጅማሬዬ።”

ከፕሮጀክት ጀምሮ ስለተጫወተባቸው ክለቦች?

ስጀምር በተለምዶ አሮጌሜዳ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ የተለያዩ ፕሮጀክቶች ነበሩ ከነሱ ነው የጀመርኩት ከዛም ወደ ሀዋሳ ተስፋ ቡድን 2004 እስከ
2006 ቆየው ከዛ ወደ ስልጤ ላፍሮ አንድ አመት ቆየው 2008 ሀላባ ገባው እዛ ነው በደንብ የእግር ኳስ ጅማሬዬን ያሳመርኩት እዛም እያለው ለወጣት ብሔራዊ ቡድን ተመርጫለሁ።ከዛ ወደ ሲዳማ ቡና ለመምጣት ችያለሁ።

ላንተ የእግር ኳስ ጅማሬ አርዓያዬ ነው የምትለው ተጫዋቾች ?

ለጅማሮዬ መነሻ ሀዋሳ ከነማ ብዙ አመት ተጫውቶ ያሳለፈውን ሙሉጌታ ምህረትን ነው እያየው ያደኩት የምንጫወትበት ቦታ አንድ አይነት ስለሆነ በስነምግባር ደረጃ ባንነፃፀርም አሁን ላይ የሙልዬን ባህሪ ነው ይዤጠነው መጫወት እምፈልገው።

በ2011 ዓም በሊጉ ዋንጫ ለማንሳት ከጫፍ ደርሳቹ አልተሳካላችሁምበ 2012 ሊጉ እስከተቋረጠበት ድረስ ተፎካካሪ ነበራቹ በዘንድሮ አመትስ ከሲዳማ ቡና ጋር በግልህ አስበሃል?

“2011 በህይወቴ የማልረሳው እና የምቆጭበት አመት ነው። በሲዳማ ቡና ታሪክ በአሰልጣኝ ዘርአይ ሙሉ ስብስብ ውስጥ በነበርኩበት አመታት በመቐለ 70 እንድርታ በአንድ ነጥብ ተበልጠን ዋንጫ ያጣንበትጊዜ በህይወቴ የማይረሳኝ ጊዜ ነበር። በአለም እና በሀገራች በኮቪድ 19 በመከሰቱ ምክኒያት ሊጉ እስኪቋረጥ ድረስ የዋንጫ ተፎካካሪ ነበር።በዘንድሮ አመት ከሲዳማ ቡና ጋር የምቀጥል ከሆነ የተሻለ ነገር እሰራለው ብዬ አስባለሁ ።

ከቡድን ጓደኛህ አበባየው ዮሐንስ ጋር ቅጣትምት እየተፈራረቃቹ ለመምታት ስትፎካከሩ ትታያላችሁ ? ከቅጣትምት ጋር በተገናኘ ምን አይነት ተሰጥኦ ነው ያለህ ?

“አበባየው ቅጣትምት በመምታት ከኔ የተሻለነው። የቅጣት ምት ሳጥን ውስጥ የሚገኙ ኳሶችን ከኔ በተሻለ ይጠቀማል።ከዛ ራቅ ያሉ ኳሶችን እኔ ሀብታሙም ግርማም አለ በመግባባት ነው የምንጠቀምባቸው ። ”

በብሔራዊ ቡድን ደረጃ ለመጫወት እቅድህ ምን ይመስላል ?በዘንድሮ አመት ከሲዳማ ቡና ጋርስ ያለህ ቆይታ?

” የሁሉም ተጫዋች ፍላጎት በብሄራዊ ቡድን ደረጃ መጫወት ነው።
በዘንድሮ አመት አስፈላጊውን ቅድመ ዝግጅት በማድረግ ለናሽናል ቲም ተመርጬ እንደምጫወት ተስፋ አደርጋለሁ።
የሲዳማ ቡና ቆይታዬ አሁን ላይ እርግጠኛ ሆኜ መናገር ባልችልም ልቤ ግን ሲዳማ ቡና ነው ያለው።”

በኢትዮጲያ ፕሪምየር ሊግ ቢያሰለጥነኝ ምትለው አሰልጣኝ?

” ጥሩ ጥያቄ ነው የጠየቅሽኝ! ለኔ ትልቅ አሰልጣኝ ዘርአይ ሙሉ በጣም ነው የምወደው የማከብረው።ከዘርአይ ቀጥሎ ቢያሰለጥነኝ ደስ የሚለኝ አሰልጣኝ ውበቱ አባተ ነው።እጅግ በጣም እማከብረው አሰልጣኝ ነው። ”
ብዙ ግዜ ከማን ጋር ተጣምረህ ስትጫወት ነው ደስ የሚልህ?
“አብሬው ብጫወት እና ጥሩ ነገር አደርጋለው ብዬ እማስበው ዳዊት ተፈራ ነው። ሌላው አንድ ቡድን ብንሆን እና አብሬው ብጫወት ደስ የሚለኝ ፍሬው ሰለሞን /ጣቀሩ/ ነው። ለቡድኑ በጣም ታጋይ ነው ይሰራል ይለፋል ከሱ ጋር ብጫወት ደስ ይለኛል።”


በጨዋታ ሊይ ፈትኖኛል የምትለው ተጫዋች ?

“አሁን ላይ ማስታውሰው የፈተነኝ ተጫዋች የለም።ሀገራችን ላይ ብዙ ጎበዝ ተጫዋቾች አሉ ይሄን ያህል ፈትኖኛ የምለው አልገጠመኝም።”

ከሀገር ውስጥ እንዲሁም ከውጪ ከተጫዋቾች የማን አድናቂ ነህ ?

“አብሮኝ የሚጫወተው ዳዊት ተፈራ በጣም ነው እምወደው እማደንቀው ሌሎችም ሲዳማ ቡና እሚጫወቱ ለምሳሌ ፈቱዲን ጀማልም በአቅም ደረጃ ጎበዝ ነው።
ከውጪ የአርሰናል ደጋፊ ነኝ የቀድሞ ተጫዋቾች የነበረው አማካዩ የፋብሪጋስ አድናቂ ነኝ ። ፖል ፖግባም ደስ ይለኛል።”
የግል ህይወትህ ምን ይመስላል አግብተሃል?
“አላገባሁም የፍቅር ጓደኛ ግን አለችኝ እንደ እግዚአብሔር ፍቃድ በዘንድሮ አመት ነገሮች ቦታ ቦታቸውን ይይዛሉ።”

ማመስገን የምትፈልገው አካል ካለ እድሉን ልስጥህ

” በቅድሚያ እዚህ ለመድረሴ ትልቁን ድጋፍ ሲያደርግልኝ የነበረው ወላጅ አባቴ ነው ። በሞተር እኔ ያለሁበት አካባቢ ሁሉ እየተከተለ ያበረታታኝ ነበር።
ሌላው አቶ ኤፍሬም ከሀዋሳ ተስፋ ቡድን በለቀቅንበት ወቅት ሰብስቦ ለዚህ እንድንደርስ ስላደረገኝ እና በዙሪያዬ ለነበሩት ሁሉንም ማመስገን እፈልጋለሁ ።