የአሌክስ ተሰማ ማረፊያ ታውቋል!

 

አሌክስ ተሰማ ስሑል ሽረን ተቀላቅሏል።

ከመቐለ 70 እንደርታ ጋር ድንቅ አመታትን ያሳለፈው ተከላካዩ አሌክስ ተሰማ በርካታ ተጫዋቾችን ያጣው ስሑል ሽረን ተቀላቅሏል። ተጫዋቹ መቐለ 70 እንደርታ ወደ ፕሪምየር ሊጉ እንዲያድግ ከማድረጉ ባሻገር በሊጉ ድንቅ እንቅስቃሴን ከሚያደርጉ ተጫዋቾች ተርታ ስምን ማሰለፍ የቻለ ተጫዋች ነው። በአሰልጣኝ ሲሳይ አብርሀም የሚመራው ስሑል ሽረ በ2013 የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ውድድር ድንቅ እንቅስቃሴን ያደርጋል ተብሎ ይጠበቃል።

Editor at Hatricksport

Facebook

ዮሴፍ ከፈለኝ

Editor at Hatricksport