የድሬዳዋ ከተማ ዋና አሰልጣኝ ፍሰሃ ጥዑመልሳን በ2013 ዓ.ም የዉድድር ዘመን አብረዋቸው የሚሰሩ ምክተሎቻቸውን አሳወቁ፡፡

 

አምና የቀድሞ የክለቡ አሰልጣኝ ሲምዖን አባይ ከክለቡ መሰናበታቸውን ተከትሎ ቡድኑን በጊዜያዊነት ይዞ የነበረው ፍሰሃ ጥዑመልሳን ዘንድሮ በዋና አሰልጣኝነት ከተሸመ ቡኃላ አብረዋቸው የሚሰሩ ምክትሎቻቸውን ይፋ አድርገዋል፡፡

በዚህም መሠረት የክለቡ ቴክኒክ ኮሚቴ በመሆን ሲያገለግል የነበረው ቶፊቅ ኢደሪስ ም/አሰልጣኝ ሲሆን ክለቡ በአዲስ መልክ በ1997 ዓ.ም ሲመሰረት ተጫዋች በመሆን ያሳለፈው ኤፍሬም ጌታሁን ሶስተኛ አሰልጣኝ መሆናቸውን አሳዉቀዋል፡፡

ም/አሰልጣኝ በመሆን የተመደቡት ቶፊቅ ኢድሪስ ከድሬዳዋ ከተማ ዉጭ ናሽናል ሲሚንትን በከፍተኛ ዲቪዚዮን በም/አሰልጣኝነትና በዋና አሰልጣኝነት አገልግሏል ቶፊቅ በተጨማሪም የኮተን ቡድን በድሬዳዋ ከፍተኛ ዲቪዚዮን የሶስት ዋንጫ ባለቤት እነዲሆን ያስቻለ አሰልጣኝ ነው፡፡

ሶስተኛ አሰልጣኝ በመሆን የተመደቡት ኤፍሬም ጌታሁን የድሬዳዋ ምርጥ ቡድኖችን በማሰልጠን በተለያዩ የክልል ሻምፒዮና ላይ የተሳተፈ ሲሆን ከዚህ ዉጭም የአሊሃብቴ እና ቀበሌ 06 ቡድኖችን ማሰልጠን ችሏል፡፡

ዘንድሮ ዋና አሰልጣኝ በመሆን የተሸሙት አሰልጣኝ ፍሰሃ ጥዑመልሳን ከም/አሰልጣኞቻቸው ጋር በመሆን ቡድኑን የሊጉ ተፎካካሪ ያደርጋሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡

Hatricksport website Editor

Twitter

kidus Yoftahe

Hatricksport website Editor