ባዬ ገዛኸኝ በመጨረሻም የባህርዳር ከነማ ንብረት መሆኑ ተረጋግጧል

 

*.. ከዋሊያዎቹ በጉዳት እረፍት የተሠጠው ባዬ
ለፊርማ እንዴት መጣ የሚለው እያነጋገረ ነው…

በኢትዮጲያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ጽ/ቤት ተገኝቶ ያልፈረመ ተጨዋች ለሌላ ክለብ ቢፈርምም መጀመሪያ አስፈረምኩ በሚለው ክለብ ሊከሰስ አይችልም.. ተጨዋቹም ያስፈረመው ክለብ ሃሳቤን ለውጫለሁ ቢል ክለቡን መክሰስ አይችልም ይሄ በቅርብ አመታት የተጀመረ አካሄድ ግን በሚገርም ሁኔታ የተጨዋቾችን የቱሪስት ፊርማ እያሳየን ነው.. ፌዴሬሽን ሳይሄዱ ሁለት ክለቦች ጋር ሄደው ፈረሙ የሚለው ዜና የተለመደ ሆኗል፡፡

ከደቂቃዎች በፊት የደረሰኝ የባዬ ገዛኸኝ ፊርማ ግን በዝውውር ሃትሪክ የሰራ መሆኑን አሳይቷል፡፡ ፌዴሬሽን ሳይመጣ የወላይታ ዲቻውን ውል ማደሱን በፊርማው አረጋገጠ ከሳምንታት በኋላ ደግሞ የተሻለ አቀረበልኝ ላለው ወልቂጠ ከተማ ፈረመ፡፡

የዝውውር መስኮቱ ሲከፈት ማጽናት የሚጠበቅባቸው ወልቂጤዎች ግን ዛሬ ሌላ ተጨዋች ፊርማ ሊያስፈርሙ ፌዴሬሽን ጽ/ቤት ሲገኙ ፈርሞልናል ያሉት ባዬ ገዛኸኝ አካሄዱን ላወቀበት ባህርዳር ከተማ ፊርማውን አኑሮና የአሰልጣኝ ፋሲል ተካልኝ ህጋዊ ተጨዋችነት አረጋግጦ ሲወጣ ተገናኙ…እንዴት ብሎ እንዳመለጣቸው እግዜር ይወቀው ብሎኛል ምንጬ…እናም የዝውውር ፊርማውን በሀትሪክ ያጸናው ባዬ የባህርዳር ከተማ ንብረት ሆኗል፡፡

ከባዬ ዜና ሳንወጣ ህመም ገጥሞኛል በሚል በአሰልጣኝ ውበቱ አገግመህ ና ፍቃድ ያገኘው ተጨዋቹ ለፊርማው ሲባል እንዴት መጣ የሚለው አነጋጋሪ ሆኗል፡፡ የተጨዋቹ ስልክ ዝግ በመሆኑ ግን ምላሹን ማግኘት አልተቻለም፡፡

Editor at Hatricksport

Facebook

ዮሴፍ ከፈለኝ

Editor at Hatricksport