በሴካፋ ከ17 አመት በታች የደመቁ ሁለት ተጨማሪ ተጫዋቾች የሊጉን ክለብ ተቀላቀሉ።
ከሰዓታት በፊት እንደነገርናችሁ የኢትዮጵያ ከ17 አመት በታች ብሔራዊ ቡድን አምበል ቢኒያም አብርሃ እና አጥቂው ዳዊት ካሳው ለፕሪምየር ሊጉ ክለብ ሸገር ከተማ መፈረማቸውን ገልፀንላችሁ የነበረ ሲሆን አሁን ደግሞ የቡድኑ ግብ ጠባቂ ተመስገን ከበደ እና የተከላካይ ስፍራ ተጫዋቹ ዘላለም መንግሥቱ በብሔራዊ ቡድኑ እና በሸገር ከተማ የፊትነስ አሰልጣኝ በሆኑት ዶክተር ዘሩ በቀለ ትልቅ ጥረት ሸገር ከተማን ተቀላቅለዋል።
ተጫዋቾቹ በቀጣዩ መጋቢት ወር በሞሮኮ በሚደረገው በአፍሪካ ከ17 አመት ዋንጫ ኢትዮጵያን ወክለው ሲወዳደሩ የውጪ ዕድል የሚያገኙ ከሆነ ለሁለት አመት ለሸገር የፈረሙት ውል ተሰርዞ ወዳገኙት ዕድል መሄድ እንዲችሉ በውሉ ላይ የተቀመጠ አማራጫቸው ሆኗል። ሀዋሳ ከተማ ፣ ኢትዮጵያ ቡና እና ባህርዳር ከተማ ሌሎች ተጫዋቾችን ለማስፈረም ጥረት ላይ የሚገኙ ክለቦች መሆናቸውንም ስምቻለሁ።


