በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የተጠበቀውን ያህል ውጤታማ አልሆነም በሚል የሸገር ሲቲ አመራሮች ለአሰልጣኞቹ ማሳሰቢያ ሰጠ።
ሸገር ሲቲ በአሰልጣኝ አሸናፊ በቀለ የሚሰለጥን ሲሆን በ11 ጨዋታ 3 ጊዜ አሸንፎ 3 ጊዜ አቻ ተለያይቶ 5 ጊዜ ተሸንፎ በ12 ነጥብ 14ኛ መሆኑ ለአመራሮቹ አልተዋጠም።
የክለቡ ቦርድ ባደረገው ውይይት አሰልጣኞቹ ውጤቱን እንዲያስተካክሉ ይህ የማይሆን ከሆነ ግን ርምጃ እንደሚወስድ ማሳሰቡን ከክለቡ ውስጥ አዋቂ የደረሰን መረጃ ያስረዳል።



