ሰበታና ክፍሌ ቦልተና በድጋሚ ሊገናኙ ይሆን?

 

ዋና አሰልጣኛቸው ውበቱ አባተን ለብሔራዊ ቡድን አሳልፈው የሰጡት ሰበታ ከተማዎች ለፕሪሚየር ሊግ ያበቃቸውን የቀድሞ አሰልጣኛቸውን ክፍሌ ቦልተናን ለመመለስ ያሰቡ ይመስላል።

በክለቡ ደጋፊዎች የሚወደደው ክፍሌ ቦልተና ከቀድሞ ክለቡ ጋር ዳግም ሊገናኝ የሚችልበት ዕድል እንዳለ ለክለቡ ቅርብ የሆኑ የሐትሪክ ስፖርት ምንጮች ገልጸዋል።

በማራኪ አጨዋወት የሚታወቀው ክፍሌ ቦልተና ሰበታን እንዲይዝ የክለቡ ደጋፊዎች ህልም ሲሆን አሁን ይህ ህልም ሊሳካ የሚችልበት ዕድል እንዳለ ሐትሪክ ከክለቡ ደጋፊዎች ተገንዝባለች።

ክፍሌ ቦልተና ሰበታ ከተማ ከአንድ ዓመት በፊት ወደፕሪሚየር ሊግ ሲያድግ የክለቡ አሰልጣኝ ነበረ።

Hatricksport website Editor

Twitter

kidus Yoftahe

Hatricksport website Editor