አሰልጣኝ ውበቱ አባተ ዋሊያዎቹን
ለማሰልጠን ተስማማ
ከደቂቃዎች በፊት በተጠናቀቀው ከፍተኛ ድርድር
አሰልጣኝ ውበቱ አባተ ለቀጣዮቹ 2 አመት ዋሊያዎቹን ለማሰልጠን መስማማቱ ተረጋገጠ፡፡
ትላንትና ዛሬ የአሰልጣኙ ስልክ ዝግ ቢሆንም ዛሬ ከ10 ሰዓት ጀምሮ በተካሄደ ድርድር አሰልጣኝ ውበቱ እስከ 2014 ዋሊያዎቹን ለመረከብ ተስማምቷል፡፡ ደመወዙና ሌሎች ስምምነቶችን በተመለከተ ፌዴሬሽኑ ነገ መግለጫ ይሰጣል ተብሎ ይጠበቃል፡፡ አሰልጣኙ በሰበታ ከተማ ውል ያለው በመሆኑ ህጋዊ በሆነ መንገድ ከክለቡ ጋር ይለያያል ተብሎም ይጠበቃል፡፡ አሰልጣኝ አብርሃም መብራቱን ለመመለስ ይደረግ የነበረው ግፊትም ሳይሳካ ቀርቷል፡፡