ሰበታ ከተማ ልምምድ ማቆማቸው ተሰማ !

የፕርሚየር ሊጉ ክለብ ሰበታ ከተማ በአዲሱ አሰልጣኛቸው ኢንስትራክተር አብርሀም መብርሀቱ እየተመሩ ያለፉትን ሳምንታት መቀመጫቸውን በሰበታ በማድረግ ልምምድ ሲያደርጉ መቆየታቸው ይታወሳል ፡፡

ዛሬ ከክለቡ የውስጥ ምንጮች ባገኘነው ታማኝ መረጃ የሰበታ ከተማ ተጫዋቾች በክለቡ ቃል የተገባላቸው ክፍያ አለመፈፀሙን ተከትሎ ልምምድ እንዳቆሙ ለማወቅ ተችሏል ፡፡

ሰበታ ከተማዎች በመጪው ቅዳሜ በሚጀምረው የቤቲኪንግ ኢትዮጵያ ፕርሚየር ሊግ የመጀመሪየ ጨዋታቸውን ከ ፋሲል ከነማ ጋር የሚጫወቱ ይሆናል ፡፡

Hatricksport website Editor

Twitter

kidus Yoftahe

Hatricksport website Editor