የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን የዲሲፕሊን ኮሚቴ 21, የሰበታ ተጨዋቾች የሶስት ወር ደመወዝ አልተከፈለንም የ2013 ውዝፍ ክፍያ አለን ብለው ባቀረቡት አቤቱታ ላይ ውሳኔ ሰጥቷል።
ዛሬ ይፋ በሆነው ውሳኔ ተጨዋቾቹ በሰሩበት ስራ ላይ ክፍያ የመጠየቅ መብት እንዳላቸው ገልጾ ውል አለን በማለት ብቻ ሳይሰሩ ደመወዝ ጠይቀዋል ያላቸውን የቢያድግልኝ ኤሊያስ ፣አብዱላዚዝ ተውፊቅ፣ አለማየሁ ሙለታ፣ሰለሞን ደምሴ፣ ፍጹም ገብረማርያም፣ ጌቱ ሃይለማሪያም፣ ምንተስኖት አሎና ዱሬሳ ሹቢሳ አቤቱታን ግን ውድቅ አድርጓል። ከዚህም በተጨማሪ ክለቡ ጥያቄያቸውን በተገቢነት ተቀብሎ እከፍላለሁ ያላቸውን የሃ/ሚካኤል አደፍርስና አንተነህ ተስፋዬን ክፍያና የተጨዋቾቹን አጠቃላይ የዘንድሮ ደመወዝ እስከ ሰኔ15/2014 ድረስ እንዲከፍል አዟል። በኮሚቴው ውሳኔ መሠረት ይግባኝ የመጠየቅ መብት እንዳላቸው ገልጾ ተጨዋቾቹ ግን በአስቸኳይ ወደ ስራ ገበታቸው እንዲመለሱ ትዕዛዝ ሰጥቷል።
በተባለው ቀን ካልተከፈለ የክፍያው አጠቃላይ መጠን ሁለት በመቶ በየዕለቱ እንዲከፍል፣ ከፌዴሬሽኑ ጽ/ቤት ግልጋሎት እንዳያገኝና ከውድድሩ እንዲታገድ ማዘዙን አስታውቋል። ሰበታ ከተማ ከፋሲል ከነማ ጋር የፊታችን ሃሙስ ከቀኑ 10 ሰአት ላይ ላለበት ጨዋታ ይደርሳሉ ወይ? የሚለው ጥያቄ አጓጊ ሆኗል።

አስተያየት ይስጡ