መነሻ ገጽ ሲዳማ ቡና የጨዋታ ዘገባ | የኤሪክ ካፓይቶ ሁለት ግቦች አዞዎቹን ባለድል አድርገዋል
ሲዳማ ቡናቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግአርባምንጭ ከተማዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየጨዋታ ዘገባ

የጨዋታ ዘገባ | የኤሪክ ካፓይቶ ሁለት ግቦች አዞዎቹን ባለድል አድርገዋል

አጋራ
አጋራ

የቤትኪንግ ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ከብሄራዊ ቡድን ጨዋታ መልስ በዛሬው ዕለት ወደ ውድድር ተመልሷል ። በቅድሚያ የተደረገው የ26ኛ ሳምንት ቀዳሚ ጨዋታም ሲዳማ ቡናን ከአርባምንጭ ከተማ አገናኝቶ በመጀመሪያው አጋማሽ በ11 ደቂቃዎች ልዩነት በተቆጠሩ ግቦች አዞዎቹ 2 ለ 1 አሸንፈዋል ።

ሲዳማ ቡናዎች በ25ኛው ሳምንት ጨዋታ ባህርዳር ከተማን 3 ለ 1 በረቱበት ጨዋታ ከነበረው የመጀመሪያ አሰላለፍ ተስፋዬ በቀለን እና መሀሪ መናን በጊት ጋትኩት እና ሰለሞን ሀብቴ ምትክ ሲያሰልፉ በአርባምንጭ ከተማ በኩል ደግሞ በሳምንቱ ከወላይታ ድቻ ጋር ያለ ግብ አቻ ከተለያዩበት ጨዋታ ከነበረው ምርጥ 11 አቡበከር ሻሚልን እና ኤሪክ ካፓይቶን በሙና በቀለ እና በላይ ገዛኸኝ ምትክ አሰልፈዋል ።

በጨዋታው የመጀመሪያ አጋማሽ የመጀመሪያ ደቂቃዎች ላይ አርባምንጭ ከተማዎች በተሻለ እንቅስቃሴ መጀመር የቻሉት ሲሆን ደቂቃዎች እየገፉ በሄዱ ቁጥር ግን ሲዳማ ቡናዎች ወደ ጨዋታው በመመለስ ከተጋጣሚያቸው የተሻለ እንቅስቃሴን ማድረግ ችለው ነበር ።

የጨዋታው የመጀመሪያ የግብ ዕድል 16ኛው ደቂቃ ላይ የታየ ሲሆን ይገዙ ቦጋለ ከፍሬው ሰለሞን በጥሩ ሁኔታ የደረሰውን ኳስ ወደ ግብ ሞክሮ በግብ ጠባቂው ይስሀቅ ተርረ በቀላሉ ተይዞበታል ።

ሲዳማ ቡናዎች ኳሱን ተቆጣጥረው በመጫወት የአርባምንጭ ከተማ የተከላካይ መስመርን ለማስከፈት ጥረቶችን ማድረግ ችለው ነበር ።

ከውሀ እረፍት መልስ 27ኛው ደቂቃ ላይ ይገዙ ቦጋለ ያገኘውን ኳስ ሳይጠቀምበት ቀርቷል ። ከሶስት ደቂቃዎች በኋላም ከማዕዘን የተሻገረን ኳስ ያኩቡ መሀመድ በግንባር በመግጨት ዘደ ግብ የላው ኳስ በግብ ጠባቂው ተመልሷል ።

በተወሰደባቸው ብልጫ በራሳቸው የሜዳ ክፍል መቆየትት የተገደዱት አዞዎቹ በ33ኛው ደቂቃ ላይ የመጀመሪያ ኢላማውን የጠበቀ ሙከራቸውን ወደ ግብነት ቀይረዋል ። ግቡን ያስቆጠረው ኬንያዊው ኤሪክ ካፓቶ ሲሆን ከእንዳልካቸው መስፍን የደረሰውን ግሩም ኳስ በግንባር በመግጨት ነበር ከመረብ ያሳረፈው ።

ጨዋታው ቀጥሎ 37ኛው ደቂቃ ላይ ሲደርስ ሲዳማ ቡናዎች አቻ መሆን ችለዋል ። አማኑኤል እንዳለ በፈጣን እንቅስቃሴ በሳጥኑ የቀኝ አቅጣጫ ይዞ የገባውን ኳስ ወደ መሀል ሲቀንሰው ጥሩ አቋቋም ላይ የነበረው አንጋፋው አጥቂ ሳልሀዲን ሰይድ ኳስ እና መረብን አገናኝቷል ።

በአራት ደቂቃዎች ልዩነት ሁለት ግቦችን ያስመለከተን አጋማሹ ከአምስት ደቂቃዎች በኋላ ሌላ ግብ ተቆጥሮበታል ። የሲዳማ ቡናው ተጫዋች ያኩቡ መሀመድ በሳጥን ውስጥ ሆኖ ኳስ በሚቀበልበት ጊዜ በሚገባ መቆጣጠር ሳይችል ኤሪክ ካፓይቶ ነጥቆት ለማለፍ ሲሞክር በሰራበት ጥፋት የፍፁም ቅጣት ምት እንዲሰጥ ሆኗል ። ኤሪክ ካፓይቶም ለራሱ እና ለቡድኑ ሁለተኛውን ግብ ማስቆጠር ችሏል ።

የመጀመሪያው አጋማሽም በአርባምንጭ ከተማ የ2 ለ 1 መሪነት ተጠናቋል ።

በሁለተኛው አጋማሽ በመመራት ላይ የነበሩት ሲዳማ ቡናዎች የተሻለ ኳሱን ተቆጣጥረው በመጫወት የግብ ዕድሎችን ለመፍጠር የሞከሩ ሲሆን በአንፃሩ አርባምንጭ ከተማዎች ከኳስ ጀርባ በቁጥር በርከት ብለው በመገኘት የሲዳማ ቡና የማጥቃት ሂድት እንዳይሰምር ለማድረግ ጠንካራ እንቅስቃሴን ማድረግ ችለዋል ።

በ56ኛው ደቂቃ ላይ አርባምንጭ ከተማዎች በፈጣን መልሶ ማጥቃት ወደ ተጋጣሚያቸው የሜዳ ክፍል በሚደርሱበት ጊዜ ያኩቡ መሀመድ በኤሪክ ካፓይቶ ላይ ጥፋቶ መስራቱን ተከትሎ በሁለተኛ የቢጫ ካርድ ከሜዳ ተሰናብቷል ።

ቀሪ ደቂቃዎችን በጎዶሎ ተጫዋቾች ለመጨረስ የተገደዱት ሲዳማ ቡናዎች በሳልሀዲን ሰይድ አማካኝነት ጥሩ ጥሩ የማግባት ዕድሎችን ለመፍጠር ችለውም ነበር ።

ሳልሀዲን ሰይድ በ63ኛው ደቂቃ ላይ በቀኝ አቅጣጫ በረጅም የደረሰውን ኳስ መሞከር ቢችልም ኳሱ ኢላማውን የጠበቀ አልነበረም ። ከአራት ደቂቃዎች በኋላም ከርቀት የተገኘውን የቅጣት ምት አጥቂው በቀጥታ ወደ ግብ ሞክሮት በግብ ጠባቂው ይስሀቅ ተገኝ ተመልሶበታል ።

በቀጣዩቹ ደቂቃዎች ጨዋታው ከግብ ሙከራዎች ርቆ የቀጠለ ሲሆን በአርባምንጭ ከተማ በኩል በፈጣን መልሶ ማጥቃት እና ረጃጅም ኳሶች መሪነታቸውን ለማስፋት ሲጥሩ በሲዳማ ቡና በኩልም ኳሱን ይዘው በመጫወት የአዞዎቹን የኋላ ክፍል ለማስከፈት ቢጥሩም ይስሀቅ ተገኝን የፈተነ የግብ ሙከራ ማድረግ ሳይችሉ ጨዋታውን አጠናቀዋል ።

ውጤቱን ተከትሎ አርባምንጭ ከተማ ነጥቡን 34 በማድረስ ወደ 7ኛ ደረጃ ከፍ ሲል ሲዳማ ቡና በበኩሉ በ40 ነጥብ በነበረበት 3ኛ ደረጃ ላይ ለመቆየት ተገዷል ።

በ27ኛ ሳምንት ጨዋታዎች በመጪው ሰኔ ( 12 ) ዕሁድ ከቀኑ 7:00 ጀምሮ አርባምንጭ ከተማ ከድሬዳዋ ከተማ ሲጫወት በዕለቱ ቀን 10:00 ጀምሮ ደግሞ ሲዳማ ቡና ጅማ አባጅፋርን የሚገጥም ይሆናል ።

አጋራ

አስተያየት ይስጡ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ተዛማጅ ጽሑፎች
ኢትዮጵያን በውጪዜናዎች

በካናዳ የኢትዮጵያዊያን የባህል እና ስፖርት ሊግ በይፋ ተመሠረተ

በካናዳ የኢትዮጵያ የባህል እና ስፖርት በሚል ስያሜ ሊግ ተቋቋመ። የኢትዮጵያን ባህል ለአለም...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየዲሲፕሊን ውሳኔዎችዲሲፕሊን ውሳኔ

የ32ኛ ሳምንት የዲሲፕሊን ውሳኔዎች

የዲሲፕሊን ውሳኔዎች አህመድ ረሺድ (ድሬደዋ ከተማ) : በኢትዮጵያ ዋንጫ ውድድር 1 እንዲሁም...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየጨዋታ ዘገባ

ሀምራዊ ለባሾቹ እና የጣና ሞገዶቹ ጣፋጭ ሦስት ነጥብን ወደ ቋታቸው ከተዋል

በሊጉ የሳምንቱ የሁለተኛ ቀን ጨዋታ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ እና ባህርዳር ከተማ ወሳኝ...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየጨዋታ ዘገባ

ሲዳማ ቡና ሲሸነፍ በተጠባቂው ጨዋታ መቻል በጎል ፌሽታ ነገሌን ረቷል

በሳምንቱ የመጀመሪያ ቀን ጨዋታ የሊጉ መሪ ሲዳማ ቡና በሀድያ ሆሳዕና ሽንፈት ሲያስተናግድ...