መነሻ ገጽ ቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ሲልቭያን ግቦሆ የ18 ወራት እገዳ ተላልፎበታል
ቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግአፍሪካወልቂጤ ከተማዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግዲሲፕሊን ውሳኔ

ሲልቭያን ግቦሆ የ18 ወራት እገዳ ተላልፎበታል

አጋራ
አጋራ

አይቮሪኮስታዊው የወልቂጤ ከተማ ግብ ጠባቂ ሲልቭያን ግቦሆ ሀገሩ ላለባት የ2022 የአለም ዋንጫ ማጣሪያ ጨዋታ በስብስቡ ውሰጥ ተካቶ በነበረበት ጊዜ በተወሰደ ናሙና ትራይሜታዚዲን የተባለ እና በአለም አቀፉ የፀረ አበረታች መድኃኒት ኤጀንሲ ( WADA ) የተከለከለ ንጥረ ነገር ተጠቅሞ በመገኘት በጊዜያዊነት ከማንኛውም ስፖርታዊ ውድድሮች ታግዶ መቆየቱ ይታወሳል ።

ጉዳዩን ሲመረምር የቆየው የአለም አቀፉ የእግር ኳስ የበላይ አካል ( FIFA ) ዲሲፕሊን ኮሚቴ ተጫዋቹ ንጥረ ነገሩን መጠቀሙ በምርመራ ከተረጋገጠበት ቀን ጀምሮ የሚታሰብ የ18 ወራት እገዳን አስተላልፎበታል ። በዚህም መሰረት እስከ ሰኔ 16 2015 ዓ.ም ድረስ በየትኛውም የፊፋ እውቅና ባላቸው የእግርኳስ ውድድሮች ላይ መሳተፍ አይችልም ።

ግብ ጠባቂው የውድድር ዓመቱ ከመጀመሩ ቀደም ብሎ ለሰራተኞቹ በመፈረም በተከታታይ 8 የመጀመሪያ ጨዋታዎች ላይ ተሰልፎ 5 ግቦችን አስተናግዷል ።

በተጨማሪም በአይቮሪኮስት ብሄራዊ ቡድንም ለተከታታይ አመታት በቋሚ ግብ ጠባቂነት የተጫወተ ሲሆን በ2015 የአፍሪካ ዋንጫን ያሸነፈው የዝሆኖቹ ስብስብ አባልም ነበር ።

አጋራ

አስተያየት ይስጡ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ተዛማጅ ጽሑፎች
ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየጨዋታ ዘገባ

የሊጉ መሪ ሲዳማ ቡና በዝናባማው ጨዋታ በመቻል ሲረታ የጣናው ሞገድም አሸንፏል

እጅግ በከባድ ዝናብ ታጅቦ በተደረገው ጨዋታ መቻል የሊጉን መሪ ሲዳማ ቡናን 3ለ1...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየጨዋታ ዘገባ

ሀድያ ሆሳዕና ፣ ፋሲል ከነማ እና ወላይታ ድቻ ወሳኝ ድል አግኝተዋል

በሊጉ የሳምንቱ የሁለተኛ ቀን መርሀግብር ሀዋሳ ከተማ ወደ ሊጉ መሪ የሚጠጋበትን ዕድል...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየጨዋታ ዘገባ

ፈረሰኞቹ በድል ሲቀጥሉ ንግድ ባንክ እና ድሬዳዋም አሸንፈዋል

ቅዱስ ጊዮርጊስ ተከታታይ ድሉን ወደ ቋቱ ሲከት ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከጨዋታ ብልጫ...

ዋልያዎቹዜናዎችየኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን

አንጋፋው አሰልጣኝ በስማቸው የእግር ኳስ ማሰልጠኛ አካዳሚ ሊገነባላቸው ነው

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን የቀድሞ አሰልጣኝ ኢንስትራክተር ሰውነት ቢሻውን ለማመስገን እና ዕውቅና ለመስጠት...