“የሰበታ ከተማ አመራሮች አታለውናል” የሰበታ ከተማ ተጫዋቾች

 

በ ቤት ኪንግ ኢትዮጵያ ፕርሚየር ሊግ እየተሳተፉ የሚገኙት ሰበታ ከተማዎች ስማቸው ከተጫዋቾች ደሞዝ ክፍያ ( ከስድስት እስከ ስምንት ወራት የደሞዝ ክፍያ ) ጋር በተያየዘ በተደጋጋሚ ሲነሳ ሀትሪክ ስፖርት ከክለቡ ተጫዋቾች በደረሳት መረጃ ተጫዋቾች መታለላቸውን ገልፀውልናል ።

” የገና በአልን አስመልክቶ ከ ጅማ አባ ጅፋሩ ጨዋታ በኋላ እረፍት ሲሰጠን ለግማሾቻችን ዕሮብ እንዲሁም ለተቀረነው በእለተ አርብ ደሞዛችን ገቢ እንደሚደረግልን ቃል ቢገባልንም የክለቡ ሀላፊዎች ዳግም ቃላቸውን በማጠፍ አታለውናል ” ሲል ከክለቡ የውስጥ ምንጭ ባገኘነው መረጃ ተገልፆልናል ።

በአለም ገና አቅራቢያ በሚገኘው የሀድሜስ ሆቴል ያረፉት የሰበታ ከተማ እግር ኳስ ክለብ በዛሬው ዕለት ምሽት ወደ ጅማ ለቀጣይ ዙር ጨዋታቸው ከማቅናታቸው በፊት የሽኝት ፕሮግራም ቢዘጋጅላቸውም ወደ ስፍራው ሙሉ የቡድን አባላት እንደማያቀኑ ለማወቅ ችለናል ።

የሰበታ እግር ኳስ ክለብ ተጫዋቾች በመጪው ቀናት አዲስ ነገር ካልተፈጠረ በቀር ለቀጣይ ዙር ጨዋታዎች ወደ ጅማ እንደማይጓዙ ለማወቅ ችለናል ።

Hatricksport website Editor

Twitter

kidus Yoftahe

Hatricksport website Editor