የ ቤት ኪንግ የኢትዮጵያ ፕርሚየር ሊግ የ6ኛ ሳምንት የተላለፉ ውሳኔዎች እና ያልተሰሙ ጉዳዮች !

 

የ ኢትዮጵያ ፕርሚየር ሊግ ውድድር እና አመራር በትላንትናው ዕለት ባደረገው ስብሰባ የተደረጉ ጨዋታዎችን ጨምሮ ሌሎች ከዳኞች እና ታዛቢዎች የቀረቡለትን የ ኢትዮጵያ ፕርሚየር ሊግ የጨዋታ ሪፖርቶች መርምሮ የተለያዩ ውሳኔዎችን ማስተላለፉን ይፋ አድርጓል ።

በስድስተኛ ሳምንት በተካሄዱ የ ቤት ኪንግ ኢትዮጵያ ፕርሚየር ሊግ ጨዋታዎች አስራ ሰባት ጎሎች ከመረብ ሲያርፉ ሁለት ጎሎች በፍፁም ቅጣት ምት ሲቆጠሩ የኢትዮጵያ ቡናው ሬድዋን ሁሴን በራሱ ላይ ግብ ያስቆጠረ ብቸኛው ተጫዋች ሆኖ በሳምንቱ አልፏል ።

የኢትዮጵያ ቡናው አቡበከር ናስር በሳምንቱ በ ሸገር ደርቢ ላይ ሶስት ጎሎችን በማስቆጠር በሳምንቱ ሀትሪክ መስራት የቻለ ብቸኛው ተጫዋች ሆኗል ።

በስድስተኛው ሳምንት ጨዋታዎች ሀያ አምስት ተጫዋቾች የማስጠንቀቂያ ካርዶችን ሲመለከቱ በድምሩ 161 የቢጫ ካርዶች በሊጉ ላይ ታይተዋል። የፈረሰኞቹ ግብ ጠባቂ ፓትሪክ ማታሲ ብቸኛው የቀይ ካርድ የተመለከተ ብቸኛው ተጫዋቾች ነው። በሳምንቱ እየታዩ ከሚገኙት የማስጠንቀቂያ ካርዶች ከግማሽ በላይ የሚሆኑት ከስፖርታዊ ጨዋነት / አድራጎት ውጪ በመሆን ሲሆን በዚህ ሳምንትም አስራ አራት ተጫዋቾች በዚህ ተግባር ለመመልከት ችለዋል ።

በስድስተኛው ሳምንት የሊጉ ጨዋታዎች ሀዋሳ ከተማ እና የሊጉ መሪ ሀድያ ሆሳዕና 9.50 ነጥብ በማምጣት የዚህ ሳምንት ስፖርታዊ ጨዋነት አሸናፊ መሆናቸው ታውቋል ።

በሳምቱ ከተላለፉ የዲሲፕሊን ውሳኔዎች መካከል የቀይ ካርድ መመልከት የቻለው ፓትሪክ ማታሲ የሶስት ጨዋታ ቅጣት እና የ 3,000 ብር መቀጮ እንዲከፍል ውሳኔ ተላልፎበታል ። ከዚህ በተጨማሪም ቅዱስ ጊዮርጊስ ክለብ ከ ኢትዮጵያ ቡና ጋር ባደረገው ጨዋታ ጋር አቤል ያለው ፣ ጋዲሳ መብራቴ እና ፓትሪክ ማታሲ በተለያዩ ጥፋቶች የማስጠንቀቂያ ካርድ መመልከታቸውን ተከትሎ የ 5,000 ብር ተጨማሪ መቀጮ እንዲከፍሉ ውሳኔ ተላልፎባቸዋል ።

በዚህ ሳምንት ካለፉት አምስት የጨዋታ ሳምንታት ጋር ሲተያይ የዲሲፕሊን ውሳኔዎች አነስተኛ ሆነው ሲታዩ ቅዱስ ጊዮርጊስ ብቸኛው ተቀጪ ክለብ ሆኗል ።

የፋሲል ከተማው ሱራፌል ዳኛቸው እንዲሁም የወልቂጤ ከተማው ሀብታሙ ሸዋለም አራት የማስጠንቀቂያ ካርዶችን የተመለከቱ ቀዳሚዎቹ ተጫዋቾች ናቸው ።

Hatricksport website Editor

Twitter

kidus Yoftahe

Hatricksport website Editor