መነሻ ገጽ ዜናዎች ሁለት ኢትዮጵያዊያን ሴት ዳኞች ወደ ኬኒያ ያመራሉ
ዜናዎችየኢትዮጵያ እግርኳስ ዳኞች ማህበርፊፋ

ሁለት ኢትዮጵያዊያን ሴት ዳኞች ወደ ኬኒያ ያመራሉ

አጋራ
አጋራ

የፊታችን ዕሁድ የትንሳኤ ዕለት የሚዘጋጀውን የፊፋ ሲሪየስ ካፕን በዳኝነት ለማገልገል ሁለት ዕንስት ኢትዮጵያዊያን ወደ ናይሮቢ ያቀናሉ።

በቅርቡ የወንዶች የፊፋ ሲሪየስ ካፕን በዋና ዳኝነት ኢንተርናሽናል ዳኞቹ ሀይማኖት አዳነ እና ሔኖክ አበበ በረዳት ዳኝነት ደግሞ ፋሲካ የኋላሸት እና ዘመኑ ሲሳዬነው በጥሩ ብቃት ሩዋንዳ ላይ የነበረው ውድድር መርተው መምጣታቸው የሚታወስ ሲሆን አሁን ደግሞ የትንሳኤ ዕለት መጋቢት 4 ጀምሮ ለተከታታይ አምስት ቀናት በኬኒያ ናይሮቢ እስከ አሁን አራት ሀገራት ማለትም አውስትራሊያ ፣ ህንድ ፣ ኬኒያ እና ማላዊ ይሳተፋሉ በተባለበት የፊፋ ሴቶች ሲሪየስ ካፕ ላይ በዳኝነት ለመምራት ሁለት ኢትዮጵያዊያን ሴት ዳኞች ወደ ቦታው ያመራሉ።

የ2017 የኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪምየር ሊግ ኮከቧ አዲሷ ኢንተርናሽናል ዳኛ ዮርዳኖስ ሙሉጌታ እና ኢንተርናሽናል ረዳት ዳኛዋ ይልፋሸዋ አየለ በዳኝነት እንዲያገለግሉ ተመርጠው ከሰሞኑ ወደ ስፍራው ያመራሉ ከተለያዩ ሀገራት አንድ አንድ ዳኛ በተመረጠበት በዚህ ውድድር ላይ ሁለት ኢትዮጵያዊን ኮታውን እንዲያገኙ በማድረግ የኢንስትራክተር ሊዲያ ታፈሠ ጥረት ከፍ ያለ ስለመሆኑም ተሰምቷል።

አጋራ

አስተያየት ይስጡ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ተዛማጅ ጽሑፎች
ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየጨዋታ ዘገባ

የሊጉ መሪ ሲዳማ ቡና በዝናባማው ጨዋታ በመቻል ሲረታ የጣናው ሞገድም አሸንፏል

እጅግ በከባድ ዝናብ ታጅቦ በተደረገው ጨዋታ መቻል የሊጉን መሪ ሲዳማ ቡናን 3ለ1...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየጨዋታ ዘገባ

ሀድያ ሆሳዕና ፣ ፋሲል ከነማ እና ወላይታ ድቻ ወሳኝ ድል አግኝተዋል

በሊጉ የሳምንቱ የሁለተኛ ቀን መርሀግብር ሀዋሳ ከተማ ወደ ሊጉ መሪ የሚጠጋበትን ዕድል...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየጨዋታ ዘገባ

ፈረሰኞቹ በድል ሲቀጥሉ ንግድ ባንክ እና ድሬዳዋም አሸንፈዋል

ቅዱስ ጊዮርጊስ ተከታታይ ድሉን ወደ ቋቱ ሲከት ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከጨዋታ ብልጫ...

ዋልያዎቹዜናዎችየኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን

አንጋፋው አሰልጣኝ በስማቸው የእግር ኳስ ማሰልጠኛ አካዳሚ ሊገነባላቸው ነው

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን የቀድሞ አሰልጣኝ ኢንስትራክተር ሰውነት ቢሻውን ለማመስገን እና ዕውቅና ለመስጠት...